ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር ተጥሎብናል " ሲሉ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ቅሬታ አቀረቡ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር ተጥሎብናል " ሲሉ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ቅሬታ አቀረቡ።
" ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር ተጥሎብናል " ሲሉ የቁርጥ ግብር ከፋዮች ቅሬታ አቀረቡ።

በርካታ በክልልና በመዲናዋ የሚገኙ የቁርጥ ግብር ከፋዮች፣ ለ2018 ዓ.ም የተቆረጠባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በደረሱ መልዕክቶች፣ በርካታ ነጋዴዎች ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ግብሩ በእጅጉ መጨመሩንና ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

አንዳንዶቹ የሚከፍሉት ግብር ከ15 - 25 ሺህ ብር ወደ 180 ሺህ ብር፣ ከ10 ሺህ ብር ወደ 46 ሺህ ብር ፣ ከ12 ሺህ ብር ወደ 110 ሺህ ብር ማደጉን ጠቅሰዋል።

ከፊሎቹ ግብሩ የተወሰነው በተጨባጭ የንግድ እንቅስቃሴ ወይም በሥራ እድገት ግምገማ ሳይሆን በዘፈቀደ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ሌሎች ደግሞ ከፍተኛውን ግብር ካልከፈሉ የንግድ ቦታቸው እንደሚታሸግ እንደተነገራቸውና የአቤቱታ ሂደቱም አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁኔታው ሰርቶ ለማደር ከባድ እንዳደረገባቸው አመልክተዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የግብር ግምገማው በተጨባጭ የንግድ አቅምና የገቢ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ እንዲከናወን እንዲሁም በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች