"የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ14 ሰዎች ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል" - የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

"የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ14 ሰዎች ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል" - የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ አደጋው መከሰቱን ገልጾ፣ ወደ ቦታው የተቀናጀ ቡድን ማሰማራቱን ነግሮናል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃጥበብ አባቡ በሰጡን ቃል፣ "ድንገተኛ አደጋ ነው የተከሰተው። ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የዝናብ፣ የመብረቅ ድምፅ ስለነበረ በዚያ ሳቢያ ነው የመሬት መንሸራተቱ ያጋጠመው" ብለዋል።
"14 ምዕመናን ሕይወታቸው አልፏል። አምስት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ሲሉም ተናግረዋል። "የሰላም ለኪ ዋሻ" ተንሸራቶ ይህ አደጋ የደረሰው ዛሬ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ መሆኑን አስረድተዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የ14 ሰዎች ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን፣ በአካባቢው ላይ ከዚህ ቀደም መሰል አደጋና የሚያሰጋ ነገር እንዳልነበር ገልጸዋል።
የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አመራር አደጋው መከሰቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። የጉዳት መጠኑን ለማወቅ፣ "ወደ ቦታው ቡድን ተልኳል፤ ቡድኑ ሲመለስ ብንገልጽ ይሻላል፤ ቡድኑ አልተመለሰም፤ ነገ ነው የሚመለሱት" ብለዋል።
በዞኑ የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ፣ በአደጋው የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ በአምስት ሰዎች ከፍተኛ፣ በሁለት ላይ ደግሞ መለስተኛ ጉዳት መድረሱን በይፋ አስታውቋል።
የወረዳ ዋና አስተዳዳሪውን ጨምሮ የወረዳ አስተባባሪ አመራርና የፀጥታ አመራሩ በቦታው በመገኘት ነፍስ ለማዳን መረባረባቸውን ገልጿል።
የህክምና ባለሙያዎችና ማህበረሰቡ በቦታው ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ብርቱ ትግል ማድረጋቸውን፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ለሟቱት ጸሎተ ፍትሐት፣ ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት መስጠታቸውንም አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia