የሐምሌ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የሐምሌ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
• የስኳር ዋጋ ብቻውን 39 በመቶ በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው ወርሃዊ የዋጋ ግሽበት መረጃ በሐምሌ 2018 ዓ.ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.3 በመቶ በመድረስ ካለፉት ወራት አንጻር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ማለትም ከሐምሌ 2017 ዓ.ም (13.7 በመቶ) ጋር ሲነጻጸር ጎልቶ የሚታይ ልዩነት ያለው ነው።
አገልግሎቱ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 15.7 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ ለዚህ በዋነኝነት አስተዋጽኦ ያደረጉት ደግሞ ፦
• ስጋ በ21.6%፣
• ስኳር በ39.4% ፣
• ዘይት በ20.34%፣
• ፍራፍሬ በ19.2%፣
• የወተት ተዋጽኦዎች እንቁላል በ18.9% እና አትክልት በ13.6% ጭማሪ አሳይተዋል።
በሪፖርቱ መሰረት የስኳር ዋጋ ብቻውን ከፍተኛውን 39 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
የምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችና ግሽበትም በሐምሌ ወር ወደ 14.8 በመቶ ደርሷል።
ከእነዚህ መካከል ፦
- ምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና ትራንስፖርት 15.6 በመቶ፣
- አልኮል መጠጦች እና ትምባሆ 16.0 በመቶ፣
- ሌሎች ዕቃዎችና አገልግሎቶች 19.3% ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን፣ ኮሙኒኬሽን ብቻ በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ማለትም 8.0 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ተለይቷል።
ተቋሙ ይፋ አድርጎት በነበረው የሰኔ 2018 ዓ.ም ሪፖርት አጠቃላይ ግሽበቱ 13.9 በመቶ ደርሶ እንደነበር የሚያመላክት ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ማለትም ከሰኔ 2017 ዓ.ም (13.9%) ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ነበር።
ከዚያም ቀደም ብሎ በግንቦት 2018 ዓ.ም የተመዘገበው አጠቃላይ ግሽበት 13.4 የነበረ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ማለትም ከግንቦት 2017 ዓ.ም (14.4%) ጋር ሲነጻጸር የተወሰነ መሻሻል የታየበት ወር ነበር።
የተቋሙ የሦስት ወራት ሪፖርት እንደሚያሳየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ከግንቦት እስከ ሐምሌ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በ1.9 መቶኛ ነጥብ ከፍ ብሏል፤ ከ13.4 በመቶ ተነስቶ በሐምሌ ወር 15.3% ደርሷል።
በተለይም የምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ ከ12.2 በመቶ ወደ 14.8 በመቶ በመድረስ ጎልቶ የሚታይ ጭማሪ ማሳየቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ሪፖርት ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia