የሪሚዲያል ፕሮግራም ተፈታኞች ቅሬታ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተፈታኞች ቅሬታ
በ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ሳይገለፅ በመዘግየቱ ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው።
"ፈተናውን ወስደን ከጨረስን ድፍን ሁለት ወራት ሊሞላን ነው" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "ይህን ያህል ጊዜ ውጤት ሳይገለፅ መቆየቱ ተገቢ አይደለም" ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
"ውጤት ሳይገለፅ 57 ቀናት ማለፉ ተገቢ አይደለም፣ ለድባቴና ያልተገባ ጫና ተዳርገናል" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "መንግሥት በአስቸኳይ ውጤታችንን ያሳውቀን" ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሪሚዲያል ፈተና ወጤት መቼ ይለቀቃል ሲል የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ከሪሚዲያል ፈተና ውጤት ጋር የተያያዘ የሚያወጡትን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
ከ53 ሺህ በላይ ተፈታኞች ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሪሚዲያል ፈተና መውሰዳቸውን ይታወቃል።
Via @tikvahuniversity