ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

‎" የታጠቁ ሃይሎች ድንገት በፈፀሙት ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፤ አራት ሰዎችን አግተው ወስደዋል " - የሱተንና ቡኢ ነዋሪዎች

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
‎" የታጠቁ ሃይሎች ድንገት በፈፀሙት ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፤ አራት ሰዎችን አግተው ወስደዋል " - የሱተንና ቡኢ ነዋሪዎች
‎" የታጠቁ ሃይሎች ድንገት በፈፀሙት ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፤ አራት ሰዎችን አግተው ወስደዋል " - የሱተንና ቡኢ ነዋሪዎች

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉና ንብረት መዘረፉ እንዲሁም መውደሙ ተገለጸ።

ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ትላንት ከሶዶ ዳጪ ወረዳ በኩል የገቡ የታጠቁ ሃይሎች በሶዶ ወረዳ ሱተን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ተኩስ በመክፈት ሰዎች ገድለዋል " ብለዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ‎ከሱተን ሸሽተው ቡኢ እንደሚገኙ የገለጹልን የአካባቢው ነዋሪ ፥ " ነሐሴ 19/2018 ዓ/ም ከቀኑ 5:30 ገደማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የታጠቁ ሃይሎች በከባድ መሳሪያ ጭምር ታግዘው ነው የገቡት " ብለዋል።

" ታጣቂዎቹ አከባቢውን በመክበብ ባደረሱት ጥቃት ስድስት ከመከላከያ ተመላሾችና ሚሊሻዎች እንዲሁም አንድ አርሶአደር በድምሩ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

‎" ጥቃት አድራሾቹ መንግስት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸው የታጠቁ ቡድኖች ናቸው " ያሉን ሌላኛው ከሱተን ሸሽተው ቡኢ ከተማ እንደሚገኙ የገለፁ የሱተን ነዋሪ ቡድኑ የሚገድለውን ገድሎ ካበቃ በኋላ የንግድ ቤቶችን ሲዘርፍና ሲሰበባር ቆይቶ በራሱ ጊዜ አመሻሹን ከተማውን ለቆ መውጣቱን ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደምም ይኸው የታጠቀ ቡድን በሱተን፣ ጢያና ሚካኤል ሰመሮ በሚባሉ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እንደሚያደርስ ፤ በቅርቡም የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ፤ በርካቶችም ከቄያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።

‎" ትላንት ታጣቂ ቡድኑ ለግማሽ ቀን ያክል ሱተን ከተማን ተቆጣጥሮ ነበር "  ያሉት አንድ የቡኢ ከተማ ነዋሪ፣ አሁንም ሕብረተሰቡ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆኑን በመግለፅ ‎የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን ብለዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሶዶ ወረዳ እና ምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስና ፀጥታ አመራሮች መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች