ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች መወዳደሪያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ይፋዊ ደብዳቤ፤ የመቁረጫ ነጥቡ የተወሰነው የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ እና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም መሰረት በዲፕሎማ (12+2) እና በሰርተፊኬት (12+1) የሙያ ስልጠናዎች መግቢያ ነጥብ እንደሚከተለው ተወስኗል፦

ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም ፦

◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 215 እና ከዚያ በላይ

◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 205 እና ከዚያ በላይ

◦ ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ በተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ወንድና ሴት ተማሪዎች 150 እና ከዚያ በላይ

ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም ፦

- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ

- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 195 እና ከዚያ በላይ

- ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች 180 እና ከዚያ በላይ

- ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተፈታኞች 180 እና ከዚያ በላይ

በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው፣ ይህ የተወሰነው መቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም (2018 ዓም የ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለወሰዱ) የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ ሲሆን፣ ሌሎች መስፈርቶች በዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተጠቅሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዳስ አበባ
መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች