የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአርሶ አደር ይዞታዎች ላይ ሲሰጥ የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገልግሎት ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱ…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአርሶ አደር ይዞታዎች ላይ ሲሰጥ የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገልግሎት ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ።
ቢሮው ለሁሉም የቢሮው የስራ ዘርፎች እና ለክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች ባስተላለፈው መመሪያ እንዳመለከተው ፣ በአርሶ አደር ይዞታዎች ላይ የሚሰጡ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉና እንዳይዘዋወሩ ቀደም ሲል እገዳ ተጥሎ ቆይቷል።
ይህ እገዳ የተጣለው አርሶ አደሩን ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች ለመጠበቅና የይዞታ ዋስትናውን ለማረጋገጥ በታለመ መመሪያ መሰረት እንደነበር ተገልጿል።
ይሁን እንጂ እገዳው በቆየባቸው ጊዜያት በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ክፍተቶች ሲታዩ መቆየታቸውንና ከባለይዞታዎች ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ሲቀርቡ እንደነበር ቢሮው ጠቁሟል።
እነዚህን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እና ለቀረቡ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ሲባል፣ ከነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እገዳው እንዲነሳ ቢሮው ወስኗል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ስራውን በከፍተኛ ጥንቃቄና በዲሲፕሊን እንዲያከናውኑ ቢሮው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለአርሶ አደሮች የሚሰጥ የመኖሪያ ቤት ፣ የድርጅትና የግብርና መጠቀሚያ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ላይ እግድ ጥሎ የነበረው ከጥር 5/2018 ዓም ጀምሮ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia