ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በ 2018 በጀት ዓመት 124.2 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በ 2018 በጀት ዓመት 124.2 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በ 2018 በጀት ዓመት 124.2 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።

• ተቋሙ በበጀት አመቱ ያገኘው የተጣራ ትርፍ 39.5 ቢሊየን ብር ነው።


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የ 2018 በጀት አመት ክንውን ሪፖርቱን እና የ 2019 በጀት ዓመት ዋና ዋና እቅዶችን ይፋ አድርጓል።

ተቋሚ በአሁኑ ሰዓት 21 የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን በእነዚህ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 9ሺ 730 ሜዋ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው መሆኑን ገልጿል።

ነገር ግን በማመንጨት አቅም ደረጃ እንጂ ሁሌም ይህን ያህል ሃይል ሲፈለግ የማመንጨት አቅም አለው ማለት አለመሆኑን ተብራርቷል።

ተቋሙ በበጀት አመቱ ይዞት ከነበረው እቅድ 91.88 በመቶ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ያሳወቀ ሲሆን ያገኘው ትርፍም በተቋሙ ታሪክ ከፍተኛ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ኢ/ር አሸብር ባልቻ ተናግረዋል።

ተቋሙ ካለው አጠቃላይ የኃይል ምርት ውስጥ 95 በመቶ የሚሆነው ከውኃ ኃይል (Hydro) የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪው 5 በመቶ ደግሞ ከነፋስ ኃይል የሚመነጭ ነው።

በአሁኑ ወቅት ተቋሙ በድምሩ 9,730 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው 21 የኃይል ማመንጫዎች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ 15 የውኃ ኃይል ማመንጫዎች (9,201 ሜጋ ዋት)፣ 5 የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች (504 ሜጋ ዋት)፣ 1 የእንፋሎት (Geothermal) ኃይል ማመንጫ (25 ሜጋ ዋት) ማመንጨት ችሏል።

የተቋሙ አጠቃላይ ሀብት 900.54 ቢሊዮን ብር መድርሱንና የተፈቀደ ካፒታሉ 1.3 ትሪሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 585 ቢሊዮን ብር መሆኑን ተገልጿል ኢ/ር አሸብር ገልጸዋል።

ተቋሙ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል በዋናነት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ሲሆን፣ 93.5 በመቶ የሚሆነው ለሀገር ውስጥ፣ ቀሪው 6.5 በመቶ ደግሞ ለውጭ ሀገራት ኤክስፖርት የሚደረግ መሆኑን ተቋሙ ይፋ ካደረገው መረጃ ላይ ተብራርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች