የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጠ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጠ።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ መርሃ ግብሮች ለመመዝገብ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው አሳስቧል።
ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፣ የቅድመ-ምረቃ ተመዝጋቢዎች የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳወቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት ይጠበቅባቸዋል።
ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የተመረቁ ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይም በቀድሞው 10+3 ወይም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው።
በተጨማሪም በሙያቸው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC Level 4) ፈተና ወስደው ማለፋቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ባለሥልጣኑ ገልጿል።
ለሁለተኛ ዲግሪ ለመመዝገብ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎችም በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል።
እነዚህ ተመዝጋቢዎች National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆንም እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውቋል።
ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት ሊያገለግል የሚችለው በባለሥልጣኑ የአቻ ግምት ከተሰራለት በኋላ ብቻ መሆኑን ገልጿል።
ባለሥልጣኑ " ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ መሆኑን እናሳስባለን " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia