የ2 ዓመት ከ6 ወር ህፃን አግተው 2.5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሁለት ግለሰቦች 19 ዓመት ተፈረደባቸው።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የ2 ዓመት ከ6 ወር ህፃን አግተው 2.5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሁለት ግለሰቦች 19 ዓመት ተፈረደባቸው።
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዓድዋ ከተማ፣ የ2 ዓመት ከ6 ወር ህፃንን አግተው 2.5 ሚሊዮን ብር ቤዛ የጠየቁ ሁለት ግለሰቦች በእያንዳንዳቸው 19 ዓመት ጽኑ እስራትና 300 ሺህ ብር መቀጮ ተፈርዶባቸዋል።
ማሙ ገብረህይወት ወልደኣረጋይ እና ፅጋብ ገረዝጊሄር ኣብርሃ የተባሉት ተከሳሾች፣ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሰሎሞን ግደይ የተባለውን የ2 ዓመት ከ6 ወር ህፃን ከአክሱም ከተማ አግተው ወደ ዓድዋ ወስደዋል።
ከዚያም ህፃኑን ለመልቀቅ 2.5 ሚሊዮን ብር ቤዛ መጠየቃቸውንና ከዚህ ውስጥ 700 ሺህ ብር መቀበላቸውን ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።
የማዕከላዊ ዞን ፍርድ ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ችሎት፣ በቀረቡት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መሠረት በሁለቱም ላይ የ19 ዓመት ጽኑ እስራትና የ300 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኗል።
የህፃኑ ቤተሰቦች ጉዳዩ በአጭር ጊዜ የፍርድ እልባት ማግኘቱን በመግለጽ፣ ለፖሊስ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
መረጃው የማዕከላዊ ዞን ፖሊስ ነው።
ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia