ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ይብቃኝ ! " - አቶ ጌትነት ወርቁ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ይብቃኝ ! " - አቶ ጌትነት ወርቁ
" ይብቃኝ ! " - አቶ ጌትነት ወርቁ

የእናት ፓርቲውና የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አመራር አቶ ጌትነት ወርቁ፣ "ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሴን አግልያለሁ" ሲሉ ከፖለቲካ ዓለም ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።

አቶ ጌትነት ወርቁ በላኩልን የግላቸው መግለጫ፦

"መኖሬ አስፈላጊና ጥቅም አለው ብዬ ሳምን የምችለውን ሳይኾን የማልችለውን ጭምር እያደረኩ ምን አልባትም አንድ PhD የሚያሠራ ጊዜዬን ላለፉት 6 የሚደርሱ ዓመታት ፖለቲካ ውስጥ ቆይቻለሁ።

በአራቱም ማዕዘን ለግፉዓን ድምጽ ሆነናል፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከውጭ ቀጥታ ከሚገለበጥ ከራሳችን ምድር መፍለቅ አለበት በሚል ሞግተናል።

መንግሥት ምን ቢከፋ ምን ቢከሳና ቢወፍር ቀዳሚ ተግባሩ የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ነው እያልን መክረናል፤ ሀገራችን ዴሞክራሲ ባይሰፍንና ብርቅ እንደኾነ ቢኖር እንኳን ሕዝቡ 'ፍትሕ ርትዕ መልካም አስተዳደር' ይገባዋል እያልን ጽፈናል፤ ተናግረናል፡፡ ሌላም ሌላም…

በተለይ በቅርብ ጊዜ ደግሞ ከመንግሥት ጋር ከምርጫ ተሳትፎ ጋር ተያይዞ ከመጋረጃው ጀርባ እጅግ ጠቃሚ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል። ረጂም ነው። እሥረኞችን ስለመፍታት፣ ጦርነት ስለማቆምና ፖለቲካ ስደተኞችን ዋስትና ሰጥቶ ወደ ሀገራቸው ስለመመለስ ነበር። ጠቅላይ ሚንሥትሩም በፓርላማ ተናግረውታል፡፡ ኹሉም በጥሩ ኹኔታ በሰለጠነ መንገድ እየሄደ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኮሚሽነሩ) ገብቶ/አስገብተውት እስከሚደበላልቀው፡፡ ያም ሆኖ ከነችግሩ የፖለቲካ እሥረኞች መፈታት መጀመራቸው በጎና የፖለቲካ ቆይታ ደመወዜ ይኾነኛል፡፡

ይኽን ከራስ ጥቅም ዘለል ያለ ነገር ወደፊት በማምጣት በብቸኝነት ልናድርገው የምንችለው እኛ ብቻ ነበርን፤ ያም ያኮራኛል፡፡ ጅምሯም እንድትኖር ያደረጉ አካላትን ማመስገን እፈልጋለሁ፤ ይቀጥላል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

አኹን በፖለቲካው መቆዬቴ ጥቅም አለው ብዬ አላመንኩም። መልቀቅም ፈልጌ የነበረው ከምርጫው በፊት ነበር፡፡ ምን አልባት የጀመርናት የእሥረኞች መፈታት ጉዳይ ወደኋላ እንዳትመለስ ሀሳቤን ቀየርኩ እንጂ፡፡ አዎ በአጠቃላይ ችግሮቹ ባሱ እንጂ አልቀነሱም፡፡

በዚህ ውስጥ ኖሮ የአቅምና ማደረግ ይገባ ነበር፤ ግን ሌላው በአዲስ ጉልበት ይቀጥልበት፡፡ ውስብስብ ችግሮቹ ሐዘኔን ቢያብሱትም፣ እንቅልፍ ቢነሳኝም፣ እንደሸክም ቢከብዱኝም አኹን ራሴን ከየትኛውም ፖለቲካ እንቅስቃሴ አቅቤ ለቤተሰቤ ጊዜ የምሰጥበት ነውና ይብቃኝ፡፡

በሂደቱ አብራችሁኝ የነበራችሁ የፓርቲዬ አመራሮች በተለይ በየቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ያላችሁ ወንድም እህቶቼ እንዲኹም የትብብሩ አመራሮችና በቀናነት ስታግዙን የነበራችሁ ድርጅቶች፣ ሚዲያ አካላት ኹሉ የከበረ ምሥጋናዬ ይድረሳችሁ " ብለዋል።

መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች