ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

3 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባውና አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርገው ግዙፍ የሕክምና ማዕከል «ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ» በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ሥ…

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
3 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባውና አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርገው ግዙፍ የሕክምና ማዕከል «ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ» በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ሥ…
3 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባውና አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርገው ግዙፍ የሕክምና ማዕከል «ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ» በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ሥራ ጀመረ።

በየዓመቱ ከ10,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር ይጓዙ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት እስከ 700 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ይደረግ ነበር። አሁን ግን ይህንን የውጭ ምንዛሬ ጫና እና የሕክምና እንግልት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ እውን ሆኗል።

ይህ በ3 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስትመንት የተገነባው ባለ 13 ወለል ዘመናዊ ሜዲካል ፕላዛ ከ110 በላይ የሕክምና አልጋዎችንና 8 የላቁ የቀዶ ጥገና ሕክምና ቲያትሮችን (Operating Theatres) በአንድ ጣራ ስር ያቀፈ ተቋም ነው።

በተጨማሪም ይህ ፕላዛ በምስራቅ አፍሪካ ሶስተኛ፣ በሀገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው  እንዲሁም በግል ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን አሜሪካ ሰራሽ GE ብራንድ PET-CT Scan ይዞ ስራ የሚጀምር ሲሆን ከዚህም ባሻገር Cath Lab፣ የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ የሚያስችል Heart – Lung መሳሪያ፣ MRI፣ CT -Scan እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ የካንሰር፣ የጽኑ ህክምና እና የልብ ሕክምና ቴክኖሎጂዎችን በማሟላት ከ20 በላይ የስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት አገልግሎቶችን ለመስጠት ተዘጋጅቷል።

በምረቃው ወቅት የከተማችን አስተዳዳሪ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረግ ራዕይ በመንግስት ጥረት ብቻ ሳይሆን በግሉ ዘርፍ በሚደረጉ እንደ ኒው ሊፍ ያሉ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች የሚሳካ በመሆኑ፣ የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ለሚሰማሩ ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

(ኒው ላይፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ)

ተዛማጅ ታሪኮች