7 ሚሊዮን ኮደርስ በዚህ ክረምት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

7 ሚሊዮን ኮደርስ በዚህ ክረምት
ethiocoders.et
ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ " ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል " ሲሉ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ጥሪ አቅርበዋል።
የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ እንደሚገኙ ገልጸው የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
" 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል፣ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው " ብለዋል።
እስከ ሰኔ 2018 ዓ/ም ድረስ የሰልጣኞች ቁጥር 5,005,146 ሲሆን እስከ ነሃሴ 2018 ዓ/ም ይህን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተቀምጧል፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህንን ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሂዷል።
መድረኩ የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸው የኢኒሼቲቩን ምሩቃን እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድ ላይ አገናኝቷል።
ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን የፈጠረ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተገልጿል።
መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ንግግር አድርገዋል።
የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ፤ የወጣቶች የቴክኒክና ዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው፣ የኮደሮችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤተልሔም ደሴ፣ የኢኒሼቲቩ ምሩቃን አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም በፓናል ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ወጣቶች ፦
- ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣
- በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉ፣
- በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ አበረታተዋል።
ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው።
ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ እና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።
የልምድ ልውውጥ መድረኩን በዚህ ይከታተሉ ፦ https://youtu.be/7zQ0gY90XLA?si=pTAgMXGz0VBoHV4u
እንዴት ልመዝገብ ?
ከ5 ሚሊዮን ለተሻገረው ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ለመመዝገብ 👉 ethiocoders.et ይጫኑ። የምስክር ወረቀቱ ዓለም አቀፍ እውቅና አለው።
ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia