#AddisAbaba
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#AddisAbaba
ከትራፊክ አደጋ አድራሽ አሽከርካሪዎች ውጪ የመንጃ ፈቃድ እገዳ ለጊዜው ቆሟል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን ደንብ ቁጥር 557/2016 በመተግበር በትራፊክ ደንብ ጥሰት ላይ የተለያዩ ቅጣቶችን ሲያስፈጽም ቆይቷል።
ደንቡ የአሽከርካሪዎችን የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይቀበል ወይም የተሽከርካሪ ሰሌዳ ሳይፈታ የዲጂታል የትራፊክ ቁጥጥርና የቅጣት ማስፈጸሚያ ሥርዓትን በመጠቀም የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የተዘረጋ አሠራርን ያካትታል።
የነጥብ ጣሪያ ሲሞላ ምን ይደረግ ነበር ?
በደንቡ መሠረት በተደጋጋሚ የትራፊክ ደንብ በመጣስ የነጥብ ጣሪያ የሚደርሱ አሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጫቸው እንዲታገድና የተሀድሶ ሥልጠና እንዲወስዱ ይደረግ ነበር።
በተጨማሪም ነጥባቸው ሳይሞላ አስቀድመው ሥልጠና ወስደው ነጥብ እንዲቀነስላቸው የሚያደርጉ ደንብ ተላላፊዎችም የሚመለከታቸው አሠራር አለ።
በደንቡ አንቀጽ 96(1) እና (2) መሠረት፣ አሽከርካሪዎቹ የሚያስፈልጋቸውን የእውቀትና የክህሎት ሥልጠና ወስደው የሥልጠናውን ማረጋገጫ ሲያቀርቡ እገዳቸው እንዲነሳ የሚደነግግ አሠራር አለ።
ችግሩ ምንድነው ?
ደንብ 557/2016 አገራዊ ደንብ ቢሆንም፣ በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ አለመደረጉ እና በአዲስ አበባ የሚያሽከረክሩ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ብቻ መተግበሩ የፍትሐዊነት ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣንም ይህንን የፍትሐዊነት ጥያቄ ለመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት አሳውቋል።
የመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎትም ጉዳዩን በመገንዘብ በ23/11/2018 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል።
በሰጠው ምላሽ መሠረት ተደጋጋሚ የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች የመንጃ ፈቃዳቸው ከታገደ በኋላ የተሀድሶ ሥልጠና የሚያገኙበትን ሂደት ውጤታማና ወጥ ለማድረግ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ሲዘጋጅ መቆየቱን ገልጿል።
መመሪያውም አስፈላጊውን ሂደት አልፎ በአሁኑ ወቅት ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን አሳውቋል።
ዓላማውም በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም ወጥ የሆነ አሠራር እንዲዘረጋ ማድረግ ነው።
ለጊዜው ምን ተወሰነ ?
የዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ጸድቆ እስኪላክ ድረስ፣ ከትራፊክ አደጋ ጉዳት ያደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ በነጥብ ወይም በቆይታ ምክንያት የሚደረገው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እገዳ ለጊዜው እንዲቆም ተወስኗል።
ይህም፦
- ቀደም ሲል በነጥብ ምክንያት የታገዱ አሽከርካሪዎችን፤
- በቆይታ ምክንያት እገዳ የተጣለባቸውን፣ ለምሳሌ ክፍያ ሳይፈጽሙ ለ6 ወር የቆዩ ጉዳዮችን፤
- ከዚህ በኋላ በነጥብ ወይም በቆይታ ምክንያት ሊታገዱ የሚችሉ አሽከርካሪዎችን ይመለከታል።
ነገር ግን ይህ ከትራፊክ አደጋ ጉዳት ያደረሱ አሽከርካሪዎችን አይመለከትም።
የገንዘብ ቅጣት አልተሰረዘም !
የመንጃ ፈቃድ እገዳው ለጊዜው መቆሙ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት ተሰርዟል ማለት አይደለም።
የደንብ ተላላፊዎች ያለባቸውን የቅጣት ክፍያ ሙሉ በሙሉ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ባለስልጣኑ ገልጿል።
ቀድሞ መንጃ ፈቃዳቸው የታገደ ምን ያድርጉ ?
ባለስልጣኑ ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም. ከአሽከርካሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ ቀደም ሲል የታገደ መንጃ ፈቃድ በእጃቸው ያለ አሽከርካሪዎች ፦
1. በመጀመሪያ ያለባቸውን የቅጣት ክፍያ ሙሉ በሙሉ መክፈል አለባቸው።
2. ክፍያውን ካጠናቀቁ በኋላ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መሄድ አለባቸው።
3. ማመልከቻ በማቅረብ የመንጃ ፈቃድ እገዳቸውን ማስነሳት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ ፦ የቅጣት ክፍያ ሳይጠናቀቅና የመንጃ ፈቃድ እገዳው በይፋ ሳይነሳ ማሽከርከር እንደማይቻል ጥብቅ ማሰቢያ ተሰጥቷል።
በአጠቃላይ የተወሰነው የደንብ ጥሰት ቅጣትን ማቆም ሳይሆን የመንጃ ፈቃድ እገዳውን ለጊዜው ማቆም ነው። ይህ ጊዜያዊ እገዳ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው እስኪወጣ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia