#EEU
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#EEU
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በስርቆትና በንብረት ዘረፋ ምክንያት ከ570 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ውድመት መድረሱን ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፥ ውድመቱ ትራንስፎርመሮችን፣ የኤሌክትሪክ ስርጭት መስመሮችን እና በመሬት ውስጥ የተቀበሩ የኬብል መስመሮችን መቁረጥና መስረቅን ያካትታል።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ከኃይል ሽያጭና ከሌሎች አገልግሎቶች 118.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል። ይህም የዕቅዱን 102.6 በመቶ አፈጻጸም መሆኑን ገልጿል። ከዚህ ገቢ 13.9 ቢሊዮን ብር ለመንግሥት ታክስ ገቢ ሲደረግ፣ 76.42 ሚሊዮን ብር ለማኅበራዊ ኃላፊነት ውሏል።
በተጨማሪም 638,505 አዳዲስ ደንበኞችን ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ማገናኘቱን ገልጾ፣ ከ450 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች ቆጣሪ እንዲያገኙ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ከተጋፈጣቸው ችግሮች መካከል የነዳጅ እጥረት፣ የኃይል ስርቆት፣ የመሠረተ ልማት ስርቆትና ውድመት፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም ውስንነት እና የአውታረ መረብ እርጅና ይገኙበታል።
በ55 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያረጁ የኤሌክትሪክ መከላከያ መስመሮችን የመቀየር ፕሮጀክትም 60.12 በመቶ አፈጻጸም ላይ መድረሱን ገልጿል።
በ2019 ዓ.ም ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ለማገናኘት ዕቅድ መያዙን አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia