#Hawassa
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Hawassa
ሀዋሳ ከተማ በቤንዚን ተጠቃሚ ባለ 3 እግር ባጃጅ እና በኪዩት ባጃጅ ታክሲዎች እንቅስቃሴ ላይ አዲስ የትራፊክ ስምሪትና የመንገድ ክልከላ ተግባራዊ ሊሆን ነው።
የሀዋሳ ከተማ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ከከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር፣ " በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያለመ " አዲስ የትራንስፖርት ስምሪት እና የመንገድ ክልከላ እንደሚጣል አስታውቋል።
አዲሱ አሰራር ከነገ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።
አዲሱ የትራንስፖርት ስምሪት እና አማራጭ ማቋረጫ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ) ለኪዩት ተሽከርካሪዎች ዝግ የሆኑ መንገዶች ፦
➡️ ከሼል እስከ ቀድሞ ማዘጋጃ አደባባይ (መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን)፤
➡️ ከዋርካ አደባባይ እስከ አሮጌ ገበያ (የቀድሞ ግሎባል ገራጅ) ድረስ ባለው አዲሱ የኮሪደር መንገድ እንዲሁም በዋናው ሀገር አቋራጭ መንገድ (ዋናው ሃይ ወይ) የነዳጅ የሚቀሳቀሱ ባጃጆችና ኩይት ታክሲዎች መንቀሳቀስ መሉ በሙሉ የተከለከለ ነው።
2ኛ) በነዳጅ ለሚሰሩ ባለ 3 እግር ባጃጆች የተከለከሉ መንገዶች፦
➡️ ከሜምቦ እስከ አዲሱ መናኸሪያ ፤
➡️ ከአቶቴ (ዋርካ) በቦሌ መብራት እስከ አልቶ ት/ት
➡️ ከሳውዝ ስፕሪንግ ሆቴል በመድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን አድርጎ እስከ 05 አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ድረስ ሙሉ በሙሉ ለባጃጅ ተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።
አማራጭ ማቋረጫ መስመሮች፦
✅ ከሼል እስከ የድሮ ማዘጋጃ አደባባይ (መድሐኒዓለም) ባለው የማቋረጫ መንገዶችን በተመለከተ፦
👉 ባጃጅም ሆነ ኪዩት ተሽከርካሪዎች፦
➡️ ከሼል- በቶታል ማደያ በኩል አድርጎ ወደ ጋሻው ገራጅ፤
➡️ በየሺ መብራት አድርጎ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚወስደው መንገድ፤
👉 ኪዩት ብቻ፦
➡️ በብሉናይል- በአዳነ ግርማ ወደ ኮሬም ሜዳ መስመር፤
➡️ ከፒያሳ ዳሽን ወደ ሞቢል መስመር፤
✅ ከአቶቴ ወደ አልቶ መስመር
➡️ ቦለ መብራት ማቋረጫ እና
➡️ ከጉዱማሌ ፓርክ በኮብልስቶን
✅ ከሜምቦ እስከ አዲሱ መናኸሪያ ድረስ ባለው መንገድ 7 ማቋረጫዎች ያሉ ሲሆን፦
➡️ ዩኒየን ትምህርት ቤት፣
➡️ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣
➡️ ወጣቶች ማዕከል (ሰላም ራዕይ ዓለምአቀፍ ቸርች)፣
➡️ ንግሴተ ፉራ ትምህትርት ቤት (አንተናውጋ)፣
➡️ አላሙራ ትምህርት ቤት፣
➡️ ታሪኩ ሕንፃ (አዲሱ ገበያ መግቢያ) እና
➡️ ዐባይ የጥርስ ሕክምና ናቸው።
የባለ ሶስት እግር ቤንዚን ተጠቃሚ ባጃጆች እንዲሁም የኪዩት አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው በተጠቀሱ መስመሮች ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ሀዋሳ
ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia