ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#Spain🇪🇸

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#Spain🇪🇸

በቀናት ውስጥ ከሞሮኮ ወደ ስፔን የሴውታ ግዛት በመሬትና በባህር ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞች ድንበር ጥሰው ስፔን፣ አውሮፓ ከገቡ በኋላ የስፔን መንግሥት ከ48 ሺህ በላይ ሰዎችን ወደ ሞሮኮ መመለሱን አስታውቋል።

የሀገሪቱ መንግሥት፥ ይህ በጅምላ ሆኖ ድንበር ጥሶ መግባት በሀገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የተፈጸመ "ጥቃት" ሲል ገልጿል።

በሁኔታው ወቅት በስፔን በኩል 57 አስከሬኖች መገኘታቸው ተገልጿል፤ በሞሮኮ በኩልም ተጨማሪ ሟቾች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

አንዳንዶቹ በባህር ውስጥ ሰጥመው ሲሞቱ ፤ ሌሎች ደግሞ የድንበር አጥርን ለመሻገር ሲሞክሩ በመጨናነቅ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በተጨማሪም ከድንበሩን ካቋረጡ ስደተኞች መካከል አንዳንዶቹ በሴውታ ውስጥ ሱቆችን ሲዘርፉ፣ ከተማውን ሲያተራምሱ መታየታቸው ተዘግቧል።

ሃምሌ 25 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች