ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#USA ⏳

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#USA ⏳
#USA

በአሜሪካ የ5 ዓመት ሕፃን ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ህይወቷን ያጠፋው ወንጀለኛ በገዳይ መድሃኒት ተገደለ።

በአሜሪካ አላባማ ግዛት፣ ካማሪ ሆላንድ የተባለች የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ሕጿኗን በመግደሉ የተፈረደበት ጄረሚ ትሬማይን ዊሊያምስ የተባለ የ42 ዓመት ጎልማሳ ባለፈው በሞት ተቀጥቷል።

ካማሪ በ2021 ከጆርጂያ ኮሎምበስ ከተማ ከቤቷ ከጠፋች በኋላ ምርመራው ወደ አላባማ ፊኒክስ ሲቲ ተስፋፋ። ፖሊስ ዊሊያምስ በሚኖርበት ቤት ፍተሻ ሲያካሂድ የሕፃኗ እቃዎች ተገኝተዋል፤ በመጨረሻም አስክሬኗ ከሕንፃው ምድር ቤት ተገኝቷል።

በምርመራው መሠረት ሕፃኗ ከመገደሏ በፊት ታስራ የግብረ ሥጋ ድፍረት ተፈጽሞባት ነበር፤ በመጨረሻም በመታነቅ ሕይወቷን አጥታለች።
በዊሊያምስ ስልክ ላይም ጥቃቱን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መገኘታቸው በፍርድ ሂደቱ ተገልጿል።

ዊሊያምስ እ.ኤ.አ በ2024 የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሲሆን ጥፋተኛ መሆኑን አምኖ የይግባኝ ሂደቶችን ለመተው በመምረጡ የተፋጠነ የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል። በዚህም ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ዕለት በገዳይ መድኃኒት መርፌ ተገድሏል።

የአላባማ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንደገለጸው፣ ዊሊያምስ ከዚህ በፊትም በሌሎች ሕፃናት ላይ ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን መናዘዙ ተገልጿል።

የዊሊያምስ ግድያ በተፈጸመበት በዚያው ሀሙስ ቀን በኦክላሆማ እና ቴነሲ ግዛቶችም ሁለት ሌሎች የሞት ፍርዶች ተፈጽመዋል።

በኦክላሆማ 70 ዓመቱ ካርሎስ ኩዌስታ-ሮድሪጌዝ እ.ኤ.አ 2003 ባለቤቱን ኦሊምፒያ ፊሸር በመግደሉ ሞት ተፈርዶበር ተገድሏል። የሞት ፍርዱ ከመፈጸሙ በፊት ከ20 ዓመታት በላይ ዘብጥያ ተወርውሯል።

በቴነሲ ደግሞ 66 ዓመቱ አንቶኒ ዳረል ሂንስ እ.ኤ.አ በ1985 ካትሪን ጄን ጄንኪንሰን የተባለች የ54 ዓመት የሞቴል ሠራተኛ በመግደሉ ተገድሏል። የሞት ቅጣቱ የተፈጸመው ወንጀሉ ከተፈጸመ ከ40 ዓመታት በኋላ ነው። ግለሰቡ ላለፉት 40 ዓመታት በእስር ቆይቷል።

በአሜሪካ ኦክላሆማ፣ ቴነሲ እና አላባማ በአንድ ቀን ሶስት የሞት ቅጣቶችን ተፈጽመዋል። ይህ በአሜሪካ ከረጅም ዓመታት በኋላ በአንድ ቀን ሶስት ግዛቶች የሞት ቅጣት ሲፈጽሙ የታየ ክስተት ሆኗል።

ለመጨረሻ ጊዜ ሶስት የአሜሪካ ግዛቶች በአንድ ቀን የሞት ቅጣት የፈጸሙት እ.ኤ.አ ጥር 7 ቀን 2010 ነበር። የ2026ቱ ክስተት ከ16 ዓመታት በኋላ የተደገመ ነው።

ሶስቱ የሞት ቅጣቶች በግዛቶቹ በተናጠል የተወሰኑ እንጂ በአንድ ላይ እንዲፈጸሙ ተቀናጅተው አልነበረም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሎስ አንጀልስ መጋዚን ነው ያገኘው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች