ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ማንችስተር ሲቲ ክሱን ለማሸነፍ ሁሉንም ያደርጋል ” ፌራን ሶርያኖ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ማንችስተር ሲቲ ክሱን ለማሸነፍ ሁሉንም ያደርጋል ” ፌራን ሶርያኖ
“ ማንችስተር ሲቲ ክሱን ለማሸነፍ ሁሉንም ያደርጋል ” ፌራን ሶርያኖ

የማንችስተር ሲቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፌራን ሶርያኖ የክለቡን ክስ ውሳኔ ለመቀልበስ ሁሉንም እንደሚያደርጉ ገለፁ።

“ ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ክስ ክርክር ለማሸነፍ ባለው ነገር ሁሉ ይፋለማል ” ሲሉ ተናግረዋል።

የህግ ሂደቱ ረጅም ጊዜ መውሰዱን ያስረዱት ፌራን ሶርያኖ “ ክሱ ፍፃሜውን ለማግኘት ገና ብዙ ይቀረዋል “ ብለዋል።

አክለውም ማንችስተር ሲቲ በዚህ ክስ ላይ ድል እንደሚጎናፀፍ አሁንም ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሀላፊው ዛሬ በነበረው የአውሮፓ ክለቦች ስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ ለአቻዎቻቸው ይህንኑ አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች