ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም ዳኛው አንዳች ስህተት አልሰራም “ ዣቪየር ቴባስ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም ዳኛው አንዳች ስህተት አልሰራም “ ዣቪየር ቴባስ
“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም ዳኛው አንዳች ስህተት አልሰራም “ ዣቪየር ቴባስ

“ ቴባስ ተቋሙን ተጠቅሞ ክለባችንን እያጠቃ ነው ” ሪያል ማድሪድ

ሪያል ማድሪድ የላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ስለ ክለቡ ለሰጡት አስተያየት ምላሽ ሰጥቷል።

ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ከደርቢው በኋላ ዳኞችን ተጠያቂ ማድረጉን ተችተው ነበር።

“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም “ ያሉት ቴባስ ዳኞች ላይ ጫና ማሳደር ነው አላማቸው ብለዋል።

“ ሮሜሮ በቀይ መውጣት እንዳልነበረበት አምናለሁ ሁይሰን በቀይ መውጣቱ ትክክል ነው “ ሲሉ ነው የተናገሩት።

ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ “ ቴባስ ማድሪድን ለማጥቃት ተቋሙን መጠቀሙ ተቀባይነት የለውም "ብሏል።

አክሎም “ ቴባስ የሊጉን ገፅታ ማበላሸቱን ቀጥሎበታል ፣ የላሊጋ ፕሬዝዳንት የውድድሩ ባለቤት አይደለም "ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች