ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሮናልዶ ሊጉ ደጋፊዎችን እንዲቀጣ ጥሪ አቀረበ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሮናልዶ ሊጉ ደጋፊዎችን እንዲቀጣ ጥሪ አቀረበ !
ሮናልዶ ሊጉ ደጋፊዎችን እንዲቀጣ ጥሪ አቀረበ !

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሊግ ትላንት ያልተገባ ባህሪ ያሳዩ የአል ታውን ደጋፊዎች ላይ ቅጣት እንዲጥል ጥሪ አቅርቧል።

አል ታውን ትላንት በአል ሂላል 6ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ደጋፊዎቹ ያልተገባ ባህሪ አሳይተው ነበር።

ደጋፊዎቹ የአል ሂላል ተጨዋች ሩበን ኔቬዝን ለማበሳጨት ህይወቱ ያለፈ የልብ ጓደኛውን ዲያጎ ጆታ ስም እየጠሩ አፊዘው ነበር።

ሩበን ኔቬስ ከጨዋታው በኋላ “ ከዚህ በኋላ ወደ ፈጣሪ እንደማትፀልዩ ተስፋ አደርጋለሁ “ ብሎ ተናግሯል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በበኩሉ “ ሊጉ ያልተገባ ባህሪ ያሳዩ ደጋፊዎችን መቅጣት አለበት "ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ጥሪ አቅርቧል።

ድርጊቱ ከእግርኳስ ጋር አይሄድም ያለው ሮናልዶ “ እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው ደጋፊዎች ዳግም ወደ ስታዲየም መመለስ የለባቸውም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች