ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
“ ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድኑ ለነገው የሱዳን ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

“ ለሱዳን ትልቅ ክብር አለን ” ያሉት ዮሐንስ ሳህሌ “ በደንብ የተደራጁ መሆናቸውን እናውቃለን ” ብለዋል።

ሱዳን በጨዋታው የሽግግር እግር ኳስ ልትጫወት እንደምትችል ገልፀው ለዚህም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

አክለውም “ ቡድኑ ልምድ ያላቸውን ከወጣቶች አዋህዶ ተዘጋጅቷል “ ያሉ ሲሆን “ የተሰጣቸውን ስራ መስራት ይችላሉ ብለን እናምናለን "ብለዋል።

“ ያለፈ ታሪክ ያለፈ ነው ፣ ለዚህ ጨዋታ ተዘጋጅተናል ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ዝግጁ ነን። ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

የኢትዮጵያ እና ሱዳን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነገ ምሽት 1:00 ሰዓት ደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም ይካሄዳል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች