ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ በታዳጊዎች ስታምን ኮከብ አልፎም ታማኝ ይሆኑልሃል ” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ በታዳጊዎች ስታምን ኮከብ አልፎም ታማኝ ይሆኑልሃል ” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን
“ በታዳጊዎች ስታምን ኮከብ አልፎም ታማኝ ይሆኑልሃል ” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

" ጥሩ ጤንነት ላይ ነኝ "

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪካዊ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በታዳጊዎች የማመን መርህ እንደነበራቸው ገልጸዋል።

“ በታዳጊ ተጨዋቾች አምናለሁ ” ያሉት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን “ በእነሱ ስታምን ሁለት ነገሮች ይፈጠራሉ ” ብለዋል።

ፈርጉሰን ሲያብራሩም “ እነሱ ትክክለኛ ኮከብ ይሆናል እንደ አሰልጣኝ ደግሞ ታማኝ ይሆኑልሃል “ሲሉ ገልጸዋል።

“ በታዳጊዎች ላይ ያለኝ እምነት በማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ክለቦች ሳሰለጥንም የነበር ነው “ ሲሉ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ተናግረዋል።

ስለ ጤና ሁኔታቸው የተጠየቁት ፈርጉሰን “ ከትንሽ ጉዳት በቀር ጥሩ የጤና ሁኔታ ይሰማኛል “ ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች