ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ባርሴሎና እና ማድሪድ ጨዋታቸውን መቼ ያደርጋሉ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ባርሴሎና እና ማድሪድ ጨዋታቸውን መቼ ያደርጋሉ ?
ባርሴሎና እና ማድሪድ ጨዋታቸውን መቼ ያደርጋሉ ?

የስፔን ላሊጋ የ 2026/27 የውድድር ዘመን በዚህ ሳምንት በሚደረጉ ስድስት ጨዋታዎች ይጀመራል።

ይሁን እንጂ ታላላቆቹ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ በዚህ ሳምንት ጨዋታቸውን አያደርጉም።

ሊጉ ዛሬ ምሽት 2:30 ዲፖርቲቮ አላፌዝ ከ ሄታፌ ጋር በሚያደርጉት መርሐግብር ጅማሮውን ያደርጋል።

ላሊጋው እና የስፔን ተጨዋቾች ማህበር ባደረጉት ስምምነት የመጀመሪያ አራት ጨዋታዎች ተራዝመዋል።

ይህ የሆነው በአለም ዋንጫ ፍፃሜ እና ደረጃ ጨዋታ የተሳተፉ የባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች በቂ እረፍት እንዲያገኙ መሆኑ ተገልጿል።

የወቅቱ የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎና ከስምንት ቀናት በኋላ ከኤልቼ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

የጆዜ ሞሪንሆው ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ከሰባት ቀናት በኋላ ከእስፓኞል ጋር ውድድሩን ማድረግ ይጀመራል።

አትሌቲኮ ማድሪድ በተመሳሳይ ተጨዋቾቹ በፍፃሜው የተካፈሉ በመሆኑ ጨዋታው ተራዝሞለት ነበር።

ይሁን እንጂ ካናዳዊው አርቲስት አቤል ተስፋዬ በስታዲየሙ ኮንሰርት ስለሚያዘጋጅ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ረቡዕ ያደርጋሉ።

በተጨማሪም :-
- የሪያል በቲስ እና ቫሌንሽያ ( ተጨዋቾች እንዲያርፉ )
- የሴልታቪጎ እና ኦሳሱና ( ሜዳው ዝግጁ ባለመሆኑ ) ተራዝሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች