“ ባንክ ኦፍ አሜሪካን ወደ ኢትዮጵያ መሳብ ትልቁ ስኬታችን ነው ” ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

“ ለተሳታፊዎች ታይሚንግ ቺፕ እንጀምራለን ” ዳግማዊት አማረ
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የሚቀርበው የ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው የማስጀመሪየ ስነ ስርዓት ምዝገባውን በይፋ አስጀምሯል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ “ በዚህ ውድድር 50 እና 40ሺህ ጨራሽ እንፈልጋለን “ ብለዋል
አክለውም " ባንክ ኦፍ አሜሪካን ወደ ኢትዮጵያ መሳብ እስካሁን ካደረግናቸው ሁሉ በጣም ትልቁ ስኬታችን ነው “ሲሉ ገልጸዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው በቀጣዩ ውድድር አዲስ ቴክኖሎጂ መጨመሩን አብስረዋል።
በቀጣዩ ውድድር “ ለተሳታፊዎች ' ታይሚንግ ቺፕ ' እናስተዋውቃለን " ሲሉ ዳግማዊት አማረ ተናግረዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ :-
- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ ሙሐመድ እንዲሁም
- የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።
በቀጣዩ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር 60ሺህ ተሳታፊዎችን ለመቀበል ዝግጅት እንደተደረገ ተገልጿል።
በ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ምዝገባቸውን በቴሌብር መተግበሪያ ብቻ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል።
የምዝገባ ዋጋው ምን ይመስላል ?
- ከመስቀል አደባባይ ለሚጀምረው ቀይ መነሻ 790 ብር
- ከግዮን ሆቴል ፊት ለፊት ለሚጀምረው እና የሰአት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ለሚኖረው አረንጓዴ መነሻ 950 ብር መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe