ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አርሰናል ማርቲኔሊን በዚህ ሳምንት ይሸጣል !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አርሰናል ማርቲኔሊን በዚህ ሳምንት ይሸጣል !
አርሰናል ማርቲኔሊን በዚህ ሳምንት ይሸጣል !

መድፈኞቹ ብራዚላዊውን የመስመር ተጫዋቻቸውን ጋብሬል ማርቲኔሊ የዝውውር መስኮቱ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ከመዘጋቱ በፊት እንደሚሸጡ ተዘግቧል።

የሳውዲው ሀያል ክለብ አል ሂላል ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየው ክለብ ሆኖ ይገኛል።

አርሰናል ከተጫዋቹ ዝውውር 60 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለማርቲኔሊ ቀጥተኛ ተተኪ ያመጣሉ ተብሎ ባይጠበቅም አልቫሬዝን የማስፈረም የረጅም ጊዜ ፍላጎት አላቸው።

አልቫሬዝ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልጽ ያሳወቀ ቢሆንም መሄድ የሚመርጠው ክለብ ባርሴሎና ሆኗል።

ይሁን እንጂ አትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋቹን ለባርሴሎና የመሸጥ ፍላጎት የለውም።

አትሌቲኮ ማድሪድ ለአርሰናል ከሆነ ተጫዋቹን 150 ሚልዮን ዩሮ የመሸጥ ፍላጎት አለው ተብሏል።

ተጨዋቹ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ሀሳቡን ቀይሮ ወደ እንግሊዝ ስለማምራቱ አሁንም ግልጽ አይደለም።

መረጃው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች