አርሰናል የዝውውር ሁኔታ ምን ይመስላል ?

አርሰናል የዝውውር ሁኔታ ምን ይመስላል ?
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ቪክቶር ኦሲሜንን ለማስፈረም በንግግር ላይ #እንደማይገኝ ተገልጿል።
አርሰናል ከጋላታሳራይ ጋር በሌሎች ተጨዋቾች እንጂ በኦሲሜን ዙሪያ አለመነጋገሩን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ዘግበዋል።
አርሰናል የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የአጥቂ እና ተከላካይ ቦታ ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋል ተብሏል።
የመድፈኞቹ የተከላካይ አማራጭ የአስቶንቪላው ኤዝሪ ኮንሳ መሆኑ ተነግሯል።
ክለቡ በአማራጭነት በመሐል ተከላካይ እና ቀኝ መስመር ቦታ መጫወት የሚችለውን ኳንሳህ እየተመለከተ ይገኛል።
በሌላ በኩል አርሰናል የፊት መስመሩን ለማጠናከር ጁሊያን አልቫሬዝ እና ይልዲዝን ሁኔታ እየተመለከተ ነው ተብሏል።
አርሰናል በዝውውር መስኮቱ ከሁለቱ አንዱን ተጨዋች ማግኘት ከቻሉ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe