ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ኳሱ ፊቱን ሲመታው ጉልበቱ ተጎድቷል ”

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ኳሱ ፊቱን ሲመታው ጉልበቱ ተጎድቷል ”
“ ኳሱ ፊቱን ሲመታው ጉልበቱ ተጎድቷል ”

ብራይተን በቼልሲ በተሸነፈበት ጨዋታ ተከላካዩ ማትስ ዌፈር ፊቱን በከረረ ኳስ ተመትቶ ሲወድቅ ታይቶ ነበር።

ተጨዋቹ በሰዓቱ የሰውነት ሚዛኑን ስቶ ለጉልበት ጉዳት መዳረጉን የክለቡ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት ተጨዋቹ እስከ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት ድርስ ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

“ ክስተቱ እንደ ቦክሰኛ ቡጢ ነበር ” ያሉት አሰልጣኙ “ ቦክሰኛ ቡጢ ሲያርፍበት እግሩ ከድቶት ሚዛኑን ያጣል ” ብለዋል።

“ ማትስ ላይም የተፈጠረው ይሄ ነው ኳሱ ፊቱን ሲመታው ሚዛኑን ስቶ ወድቅ ጉልበቱን ተጎዳ ነገርግን እንደ እድል ከባድ አይደለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች