ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ዋንጫ ላላሸነፈ ተጨዋች ባሎን ዶር መስጠት አይቻልም ” ሊዛራዙ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ዋንጫ ላላሸነፈ ተጨዋች ባሎን ዶር መስጠት አይቻልም ” ሊዛራዙ
“ ዋንጫ ላላሸነፈ ተጨዋች ባሎን ዶር መስጠት አይቻልም ” ሊዛራዙ

በተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው ፈረንሳዊ የቀድሞ ተከላካይ ሊዛራዙ ዋንጫ ያላሸነፈ ተጨዋች ባሎን ዶር እንደማይገባው ገልጿል።

“ ምንም ዋንጫ ላላሸነፈ ተጨዋች ባሎን ዶር አንስቶ መስጠት አይቻልም “ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

አክሎም “ ፋብያን ሩይዝ አለም ዋንጫ እና ሻምፒየንስ ሊግ በጋራ ስላሸነፈ ምርጥ ሶስት ውስጥ አካትተዋለሁ ” ብሏል።

“ ፋብያን ሩይዝ ባሎን ዶሩን ካሸነፈ ምንም አይገርመኝም ይገባዋል “ ሲል ሊዛራዙ ተናግሯል።

ስፔናዊው አማካይ ፋብያን ሩይዝ በበኩሉ “ እንደ ቡድን ሁሉንም ነገር አሸንፊያለሁ ” ሲል ገልጿል።

አያይዞም “ ከዚህ ሁሉ ሥራ በኋላ የሚገባኝን እውቅና ለማግኘት የቀረኝ እንደ ባሎን ዶር ያለ የግል ሽልማት ነዉ ” ብሏል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች