ዎት ዌግሆርስት ለምን መነጋገሪያ ሆነ ?

ዎት ዌግሆርስት ለምን መነጋገሪያ ሆነ ?
ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ዎት ዌግሆርስት ከጨዋታ በፊት እጆቹን ተጠቅሞ ያልተለመደ ነገር ሲያደርግ ነበር።
ዌግሆርስት በሰዓቱ ባደረገው ድርጊት ደጋፊዎች የቀለዱበት ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያውም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ይሁን እንጂ ዎት ዌግሆርስት ያደረገው አእምሮውን ይበልጥ ዝግጁ ለማድረግ የነርቭ ልምምድ ነበር።
ተጨዋቹ ከጨዋታው በፊት አእምሮውን ለማንቃት የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንደተጠቀመ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።
በኔዘርላንድ እውቅና ያላቸው የነርቭ ሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር ኤሪክ ሼርደር ስለ ሁነቱ ሲያስረዱ “ እጅን ለማንቀሳቀስ የአንጎላችንን ብዙውን ክፍል ይፈልጋል “ ይላሉ።
“ እጅ ሲንቀሳቀስ አብዛኛው የአንጎላችን ክፍል በቅንጅት ይሰራል “ ያሉት ባለሙያው “ ስለዚህ ያንን ሲያደርግ ብዙውን ክፍል ያነቃቃል " ብለዋል።
“ በመሰረቱ ያንን ማድረግ ስርዓቱን እንደማዘጋጀት ነው አእምሮን እንደመክፈት ነው "በማለት ተናግረዋል።
ዎት ዌግሆርስት ወደ ጨዋታው ከገባ በኋላ ወሳኝ የአቻነት ግብ በማስቆጠር ቡድኑ ቲዌንቴ ፒኤስቪን እንዲያሸንፍ ረድቷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe