ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የባሎን ዶር ድምፅ ለራሴ እሰጣለሁ ” ምባፔ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የባሎን ዶር ድምፅ ለራሴ እሰጣለሁ ” ምባፔ
“ የባሎን ዶር ድምፅ ለራሴ እሰጣለሁ ” ምባፔ

“ ሁሉንም መስፈርት ያሟላ አሸናፊ ታይቶ አያውቅም ”

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው ተናግሯል።

“ ይሄ የግል ሽልማት ነው ተጨዋቹ በግሉ ምን አደረገ የሚለውን ነው መመልከት ያለብን ለራሴ ድምጽ እሰጣለሁ “ ሲል ምባፔ ተናግሯል።

ሰዎች ዋንጫ አለማሸነፉን ማንሳታቸው " ልክ አይደለም " ያለው ምባፔ " ሁሉንም መስፈረት ያሟላ የባሎን ዶር አሸናፊ እስካሁን አልታየም " ብሏል።

“ በአለም ዋንጫ ታሪክ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን በሰዎች አይምሮ ውስጥ የሚቀመጥ ነገር ነው “ ሲል ነው ምባፔ ያስረዳው።

አክሎም “ የአለም ዋንጫ ፤ ሻምፒየንስ ሊግ ኮከቦች ያሉበት ውድድር ሁሉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነ ያለ አይመስለኝም " ብሏል።

“ ታሪክ ሰሪነት ሊያሸልም ይገባል “ የሚል እምነት እንዳለው በመግለፅ “ ካሸነፍኩ ማንንም ዘርፌ አይደለም “ ሲል ገልጿል።

“ ነገርግን በዚህ የማይስማሙ ሰዎችንም እረዳለሁ ይሄ አምባገነንነት አይደለም "ምባፔ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች