የአርሰናል እና ብራይተን ጨዋታ ምን መልክ ነበረው ?

የአርሰናል እና ብራይተን ጨዋታ ምን መልክ ነበረው ?
መድፈኞቹ በሁሉም ውድድሮች ያደረጉት መቶ ፐርሰንት የማሸነፍ ግስጋሴ ዛሬ ምሽት ተገቷል።
125ኛ አመቱን ለማክበር ያዘጋጀውን ልዩ ማልያ ለብሶ ወደ ሜዳ የገባው ብራይተን ክብረ በዓሉን በድል አጅቧል።
ባለሜዳው ቡድን ብራይተን ለአርሰናል ጠንካራ እና ለመቆጣጠር ፈታኝ ሆኖበት ተስተውሏል።
ባለፉት አስር ቀናት አራት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ ያደረገው አርሰናል በአንፃሩ ጥሩ ያልሆነ እንቅስቃሴ አሳይቶ አጠናቋል።
መድፈኞቹ በጨዋታው ያሳዩት እንቅስቃሴ ለረጅም ጊዜ ያልታየ ደካማው አቋም እንደሆነ ይታመናል።
ከዚህ ምሽት በፊት አርሰናል ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ 3️⃣ ግብ የተቆጠረበት በሁለት አጋጣሚዎች ብቻ ነበር።
አርሰናል በጨዋታው ሲቸገር የነበረ ሲሆን በመከላከል ረገድ ተጋጣሚውን ለመያዝ እና ኳስ ሲይዝ ወደፊት ለመግፋት ተቸግሮ ተስተውሏል።
ብራይተን ጨዋታውን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን አርሰናል የሚታወቅበትን አካላዊ የበላይነትም ወስዶ ነበር።
የብራይተን የፊት መስመር ዴቪ ራያ የሚልካቸውን ረጅም ኳሶች ማምከን የሚችል የኋላ መስመር እንዳለ ሲለሚያውቅ ያለ ማቋረጥ ያጠቃ ነበር።
የመጀመሪያ ሁለት ግቦችም በድንቅ የግል ብቃት ከርቀት ተሞክረው የተገኙ ነበሩ።
ከዚህ ጨዋታ በፊት አርሰናል በሊጉ የተቆጠረበት ግብ አንድ ሲሆን ዛሬ ሶስት ግቦችን ማስተናገዱ ሚኬል አርቴታን ያሰጋ ሆኗል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe