ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ !
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ !

የ 2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሐ ግብር በአሁን ሰዓት ይፋ በመደረግ ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ሳምንት መርሐ ግብር :-

- ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ነገሌ አርሲ
- ኢትዮጵያ ቡና ከ ሸገር ከተማ
- ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ ዓ.ዩ
- ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህርዳር ከተማ

- ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ
- ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል
- ጋሞ ጨንቻ ከ ኢትዮጵያ መድን
- ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታዎች መቼ ይደረጋሉ ?

ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 2️⃣ኛ ሳምንት ( አዲስ አበባ ስታዲየም )

ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ :- 4️⃣ኛ ሳምንት ( ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም )

ፋሲል ከነማ ከ ባሕር ዳር ከተማ :- 5️⃣ኛ ሳምንት ( ባሕር ዳር ስታዲየም )

በቀጣይ የሊጉ ውድድሮች በሰባት ስታዲየሞች እንደሚደረግ በመርሐ ግብሩ ተገልጿል።

አብዛኛው የሊጉ ጨዋታዎች ከ አርብ እስከ ሰኞ ባሉ ቀናቶች ሲደረጉ የ 7️⃣:0️⃣0️⃣ ሰዓት ጨዋታዎች እንደማይኖሩ ታውቋል።

የ 2018 የውድድር ዘመንን ምን ያህል ሰው ታደመ ?

የተጠናቀቀውን የ 2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን 2️⃣9️⃣1️⃣, 6️⃣6️⃣5️⃣ ተመልካቾች ብቻ ትኬት ቆርጠው በመግባት ታድመዋል።

በአዲሱ የውድድር ዘመን አራት ወደ ታችኛው ሊግ የሚወርዱ ክለቦች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ፍቃድ ያገኙ ሰባት ስታዲየሞች ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች