32 ኤርትራውያንና 3 የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአርባምንጭ ተያዙ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

32 ኤርትራውያንና 3 የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአርባምንጭ ተያዙ።
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 32 የኤርትራ ዜጎች ሁለት ተቀባይና አንድ አሽከርካሪ ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ኤርትራዊያኑ መነሻቸውን ከመሃል ሀገር በማድረግ በአርባምንጭ ኮንሶ ጂንካ በኩል ወደ ኬንያ ለመሸጋገር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የገለጹት ኮማንደር ክበበው፣ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ ክትትል በሲቀላ ክ/ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ሲያትል አልጋ ቤት ግራውንድ ስር ባለ አዳራሽ ፍራሾችን በመጣል ከተሸሸጉበት መያዛቸውን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 11 ወንዶች፣ 14 ሴቶች እና 7 ህጻናት በድምሩ 32 ኤርትራውያን ናቸው የተያዙት።
በተጨማሪ ሁለት አዘዋዋሪዎች እንዲሁም ስደተኞችን ወደ አርባ ምንጭ ያመጣ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3-23042 አአ " ሀይሩፍ መኪናና አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አዛዡ አስታውቀዋል።
በተዘዋዋሪዎቹ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንና ስደተኞቹን ለክልሉ ፖሊስ አሳልፎ የመስጠት ሂደት እንደሚከናወን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia