#Tigray
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Tigray
በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ተቋርጧል።
ሮይተርስ ፤ አራት ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ሰዎችን እና የዲፕሎማቲክ ምንጭ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረጉት የህወሓት መሪዎች ናቸው።
ምንም እንኳን ህወሓት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም አንድ ከህወሓት ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጭ " ህወሓት ነው ያቋረጠው " የሚለውን መረጃ አስተባብለዋል።
ህወሓት ኔትዎርኩን እንዳቋረጠ የገለጹ የሮይተርስ ምንጭ፤ " የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያዘዘው የመንግሥት ወታደሮች በውጊያ ድሮኖችን ሲጠቀሙ የሞባይል ኔትዎርኮችን እንዳያገኙ የተጠቀመበት ስልት አካል ሳይሆን አይቀርም " ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የስምረት ፓርቲ አመራር ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐለፎም ንርኣ " የስልክ እና ኢንተርኔት ግንኙነት (ኔትዎርክ) እንዲቋረጥ ያደረገው ህወሓት ነው " ብለዋል።
" ካሁን በፊትም ትግራይ ክልል ላይ ካለው ዋናው መስሪያ ቤት ሄደው ነበር የቆረጡት። ቆርጠው በክልሉ ባሉ ከተሞች እንዳይሰራ፣ እዛው ያሉበት ከተማ ግን እንዲያገናኝ አድርገውት ነበር በ2013 ዓ/ም " ሲሉ አስታውሰዋል።
" ስለዚህ ስለሚያውቁት ቴሌም በየብራንቹ መቆጣጠሪያ ስላለው እሱን ነው ያጠፉት " በማለት አሁን የተዘጋበትን መንገድ አስረድተዋል።
" የሳፋሪኮምም ከዚህ ጋር የተያያዘ መስሏቸው ነበር። ግን ለብቻው ነው " ብለዋል። " ዛሬ ግን 'በአስቸኳይ እንድትዘጉት' ብለዋቸዋል " በማለት ተናግረዋል።
" ህወሓት የኔትወርክ አገልግሎት እንደሚዘጋ እየተናገረ ቆይቷል። 'በቅርብ ቀን እንዘጋዋለን' እያሉ ነበር " ሲሉም አስታውሰዋል።
" ለዚህ የኔትዎርክ ማቋረጥ እንደ ዋና ምክንያት የሚያቀርቡት አንዱ ' በውስጣችን/በመካከላችን ለፌደራል መንግስት ጥቆማና መረጃ የሚሰጡ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል ' " የሚል ነው።
" በሌላ በኩል ' በድሮን ጥቃት እየደረሰ ያለው ጉዳት በኢንተርኔት የሚታገዝ ነው ' በሚል ነው የኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎት የማቋረጥ እርምጃ የወሰዱት " ሲሉ አቶ ሓለፎም የተናገሩት።
" እንደሚዘጋ አስቀድመውም እያወሩ ስለነበር እኛም ለአንዳንዶቹ የኛ ሰዎች እየተናገርናቸው ነበር " ሲሉም አክለዋል።
" የቴሌ ኔትወርክ ሲዘጋ የሳፋሪኮም አልተዘጋም ነበር። ነገር ግን ሳፋሪኮምንም የጸጥታ አካል የሆኑትን እነፍስሃ ማንጁስንና አንድን ሌላ አካል ወደ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ሄደው እንዲዘጉት አዘዋል። ቴሌ ከተዘጋ በኋላ ሰዎች በሳፋሪኮም ለመጠቀም ሲም ካርድ ለማውጣት ዛሬ ወረፋ ይዘው ነበር። ግን የሳፋሪኮምንም ሊዘጉት ስለሆነ 'አትክሰሩ አቁሙ' ተብሏል " ብለዋል።
"' ዛሬ ሳፋሪኮም ይዘጋል። ከዛሬ እንዳያልፍ' ተብሏል " ሲሉም ያጣሩትን መረጃ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia