#Update
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Update
በቀድሞ የህወሓት አመራሮች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ፣ የትግራይ ሕዝብ የማይፈልገውና የማይመኘው አዲስ ወታደራዊ ግጭት ዛሬ ሌሊት መቀስቀሱን አሳውቋል።
" ግጭቱን ማንና መቼ እንደጀመረው ለማወቅ አስቀድሞ ተዘጋጅቶ የወጣውን የኋላቀሩ ቡድን (ህወሓት) መግለጫ ከመስማት ይልቅ፣ ገለልተኛ አካላት የሚያደርጉትን የሳተላይት ክትትልና የክትትሉን ውጤት መጠበቅ ተገቢ ነው " ሲል ገልጿል።
ፓርቲው፣ " አሁን የተከፈተው ጦርነት በውጭ ኃይሎች ፍላጎትና እቅድ የሚመራና የሚደገፍ ነው " ብሏል።
" ሆኖም የጦርነቱ እቅድ በራሳቸው የጦርነት ነጋዴዎች አማካኝነት አስቀድሞ ምስጢሩ ታውቆ ያደረ በመሆኑ እንቅስቃሴው ገና ሳይስፋፋ የሚከሽፍ ነው " ሲል ጠቅሷል።
አክሎም፣ " የዚህ አላስፈላጊ ግጭት ዋና ሰለባና የመከራው ተቀባይ እየሆነ ያለው የትግራይ ወጣት መሆኑ አሳዛኝ ያደርገዋል " ብሏል።
" ይህ ቡድን የፕሪቶሪያውን የሰላም ውል በመጣስ፣ የህጋዊውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሥልጣን በኃይል ገልብጦ ህገ-ወጥ አስተዳደር መሥረቱ ሳይበቃው፣ አሁን ደግሞ 'ግዛታዊ አንድነትን ማስከበር' በሚል ሽፋን በውጭ ኃይሎች ተመክቶ አዲስ ጦርነት ደግሷል " ሲል ከሷል።
" ቀደም ሲል በተለያዩ መድረኮች ሲያካሂዷቸው የነበሩት የዛቻና የትምክህት መግለጫዎች ቡድኑ ለጦርነት የነበረውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት የሚያሳዩ በቂ ማስረጃዎች ናቸው "ም ሲል አመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፓርቲው መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ሰራዊት አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት፣ አመራሮቹ የተሻለ ወታደራዊ እውቀትና ግንዛቤ አላቸው ተብሎ ስለሚታመን ለትግራይና ለሕዝቧ የሚጠቅም የበሰለ ውሳኔ መወሰን እንደነበረባቸው አስገንዝበዋል።
" የትግራይን ሕዝብ አንድነት አበላሽታችሁ በአልቡርሃን፣ በፋኖ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በሻዕቢያ ተመክታችሁ የምታደርጉት ፎከራና ዛቻ ሕዝብን ወደ ከፋ አደጋ ከማስገባት ውጪ የምታመጡት ምንም ዓይነት ለውጥ የለም " ብለዋል።
አክለውም፣ " ደብረጽዮንና ፈትለወርቅ መርተዋችሁ፣ ጌታቸው አሰፋ መንገድ እየመራችሁ፣ በግዳጅና በግፍ ወጣቱን በመመልመል 'ወደ አራት ኪሎ እንመለሳለን' የሚለውን ቅዠት ፈጥናችሁ ልታቆሙት ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።
ለትግራይ ሠራዊት አባላት ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ፣ " ሊያሳስባችሁ የሚገባው በጣት የሚቆጠሩ ወንጀለኞች ህልውና ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ህልውና ነው " ብለዋል።
በመሆኑም ሠራዊቱ በሕይወቱና በአካሉ የሚጫወቱ አካላትን " ይበቃል " ሊላቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ሕዝቡ ያለበት የመኖርና አለመኖር የህልውና ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ሊመለስ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፣ " ልንወቀስና ልንፈራረጅ የምንችለው መጀመሪያ እንደ ሕዝብ በሕይወት ስንኖር ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።
በሃውልቲ የመሸገው ቡድን የዲፕሎማሲ በሮችን በሙሉ ዘግቶ፣ ያለ በፎከራና ከውጭ አካላት በሚጠበቅ እርዳታ ተመክቶ ሁኔታዎችን ካበላሸ በኋላ " ዓለም ስማኝ "የሚል ጩኸት ማሰማቱ፣ የአመራርነት ይቅርና ተራ አስተዋይነት እንኳን የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ኮንነዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 25 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia