ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#USA

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#USA
#USA

የአሜሪካ ጦር እስከ ነገ ሮቡዕ (መስከረም 30) ድረስ በኢራቅ ከሚገኙት የመጨረሻ የጦር ሠፈሮቹ ሙሉ በሙሉ ለመውጣት መዘጋጀቱ ተገለጸ።

ይህ ውሳኔ በኢራን እና በሀገሪቱ በሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ዘንድ እንደ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ድል እና የአሜሪካ ፕሮጀክት መክሸፍ ተቆጥሯል።

የኢራቅ ደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት፣ የአሜሪካ ጦር መውጣት ለቴህራን ሰፊ የመንቀሳቀስ ነፃነትን በመስጠት የፖለቲካ እና የደህንነት ተጽዕኖዋን እንዲያጠናክር የሚያስችላት ሲሆን፤ እንደ አይኤስ (ISIS) ያሉ አክራሪ ቡድኖች ዳግም እንዲያንሰራሩ በር ሊከፍት ይችላል።

አሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ከሥልጣን ለመገልበጥ እ.አ.አ መጋቢት 2003 ኢራቅን ወርራ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በቆየችበት ቆይታ ከ4,500 በላይ ወታደሮቿን አጥታለች። #ቢቢሲ

መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች