ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በፍላጎት ደረጃ ያለ እንጂ የተፈረመ እና ያተጠናቀቀ የብድር ሂደት የለም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በፍላጎት ደረጃ ያለ እንጂ የተፈረመ እና ያተጠናቀቀ የብድር ሂደት የለም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
" ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በፍላጎት ደረጃ ያለ እንጂ የተፈረመ እና ያተጠናቀቀ የብድር ሂደት የለም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

👉 አበዳሪዎች የመጨረሻ ውሳኔያቸውን እስከ መጋቢት 2019 ዓም ድረስ ባለው ጊዜ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ እየተገነባ ያለውን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሂደትን በሚመለከት በሰጠው ማብራሪያ ለግንባታው ከአበዳሪ ሃገራት እስከ 9 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የብድር መጠን የሚያስፈልግ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

ይህ ብድር ከአንድ ተቋም የሚወሰድ ሳይሆን ብዙ አበዳሪዎች የድርሻቸውን አዋጥተው በአንድ ላይ የሚያቀርቡት የብድር መጠን መሆኑን አስረድተዋል።

ለእዚህም የአሜሪካ ፣የአውሮፓ ፣የኤዢያ፣ የመካከለኛው እና የሩቅ ምስራቅ ሃገራት የፋይናንስ ተቋማት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

ለብድሩ ሂደት እንዲሆንም የአዋጭነት ጥናት ተጠንቶ ያበድራሉ ተብሎ ለሚታሰቡ ሃገራት የተላከ መሆኑን ይህም አየር መንገዱ ባጠናው ጥናት ላይ መነሻ በማድረግ የራሳቸውን የውስጥ ጥናት ካጠናቀቁ በኋላ ስለ ብድሩ ሁኔታ ውሳኔያቸውን የሚያኖሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንንም ሂደት በርካታ አበዳሪ ድርጅቶች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ከአበዳሪ ድርጅቶች ጋር በተደረጉ ውይይቶችም እስከ 8.5 ቢሊየን ዶላር ቃል መገባቱን ከእነዚህ አበዳሪ ተቋማት አንዱ እና የብድር ሂደቱ አስተባባሪ የሆነው የአፍሪካ ልማት ባንክም በግሉ እስከ 500 ሚሊየን ዶላር ቃል መግባቱን አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ለአየር መንገዱ ግንባታ ከሚውለው የብድር ሂደት ውስጥ በፍላጎት ደረጃ ያለ እንጂ የተፈረመ እና የተጠናቀቀ የብድር መረጃ የለም ያሉት አቶ መስፍን ይህ የሆነበት ምክንያትም ተቋማቱ በራሳቸው የአዋጭነት ጥናት ሰርተው ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ነው ብለዋል።

አበዳሪዎቹም እናበድራለን ያሉት ገንዘብ ለመልቀቅም እስከ የሚቀጥለው አመት 2019 መጋቢት ወር ድረስ ጊዜ ያላቸው በመሆኑ ከሁሉም አበዳሪ ተቋማት ጋር የአፍሪካ ልማት ባንክ በአስተባባሪነት እየሰራ የሚገኝ መሆኑን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 22 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች