ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

መንታ ሆና የተወለደች እናት አምስት (5) ህፃናት በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏን ባለሙያዎች ገለጹ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
መንታ ሆና የተወለደች እናት አምስት (5) ህፃናት በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏን ባለሙያዎች ገለጹ።
መንታ ሆና የተወለደች እናት አምስት (5) ህፃናት በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏን ባለሙያዎች ገለጹ።

እናቲቱ በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አበርገለ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ ሲሆኑ በየጭላ መባእታዊ ሆስፒታል አምስት ህፃናትን ወልደዋል።

የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ እናቲቱ ራሷ መንታ ሆና የተወለደች መሆኗን የሚያሳይ የህክምና ታሪክ አላት።

ከአምስቱ ህፃናት መካከል አራቱ የእድገት ሂደታቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀው የተወለዱ ሲሆን፣ አምስተኛው ህፃን ግን ከአምስተኛው ወር በኋላ የእድገት ሂደቱ በመስተጓጎሉ የተነሳ የእድሜውን እድገት ሳያጠናቅቅ መወለዱን ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።

አዋላጅ የጤና ባለሙያዎች እንዳስረዱት፣ እናቲቱም ሆነች አምስቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፣ ተገቢውን የጤና ክትትልም እያገኙ ነው።

ባለሙያዎቹ አክለውም፣ እናቲቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የወለደች መሆኗን ጠቁመው፣ አምስቱን ህፃናት በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያስችል የተመቻቸ ኑሮና በቂ ገቢ ስለሌላት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች