ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማይጨው ከተማ ሙሉ በሙሉ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነች።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማይጨው ከተማ ሙሉ በሙሉ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነች።
ማይጨው ከተማ ሙሉ በሙሉ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነች።

ከተማዋ ከዛሬ እሁድ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ጀምሮ ነው ሙሉ በሙሉ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ የሆነችው።

የኤሌክትሪክ መቋረጡ ወደ ከተማዋ ኤሌክትሪክ የሚያስተላልፉ ስድስት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታዎሮች በመውደቃቸው መሆኑን የማይጨው ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ታዎሮቹ በተፈጥሮ አደጋ መውደቃቸውን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ፣ አደጋው በደቡባዊ ዞኑ ራያ ዓዘቦ ወረዳ፣ ካራ-ዓዲሻዎ ቀበሌ በሚገኝ አካባቢ መከሰቱን ጠቁሟል።

በተመሳሳይ፣ የማይጨው ከተማና አካባቢዋ የመብራት ኃይል ቅርንጫፍ አገልግሎት ታዎሮቹ የወደቁት ንፋስ የቀላቀለ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ መሆኑን ገልጿል።

የተበላሹትን ታውሮች በአስቸኳይ ለመጠገን ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም የጥገና ሥራው ቀናት ሊወስድ እንደሚችል የአገልግሎት መስጫ ማዕከሉ አስታውቋል።

በመሆኑም ህዝቡ ጥገናው እስኪጠናቀቅ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

እሁድ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም የክረምት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ያላገኙ በርካታ አካባቢዎች ዝናብ ማግኘታቸውም ታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia            

ተዛማጅ ታሪኮች