" በ8ኛ ክፍል 155፣ በ6ኛ ክፍል 81 በድምሩ 236 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም " - አቶ አብዮት ደምሴ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በ8ኛ ክፍል 155፣ በ6ኛ ክፍል 81 በድምሩ 236 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም " - አቶ አብዮት ደምሴ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጎ ተማሪዎችም ውጤታቸውን እያዩ ነው።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በ2018 ዓ/ም 8ኛ ክፍል 86 ሺህ 502፣ በ6ኛ ክፍል 126 ሺህ 224 ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በ6ኛም ሆነ 8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ደግሞ 48 እና ከዚያ በላይ መሆኑን አቶ አብዮት አብራርተዋል።
በዚህም መሰረት አጠቃላይ 8ኛ ክፍል ከተመዘገቡ 86 ሺህ 502 ተማሪዎች መካከል 78 ሺህ 203 ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50ና በላይ እንዲሁም 48 እና በላይ ውጤት በማስመዘገብ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች 60.4 በመቶ አልያም 47 ሺህ 307 መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 126 ሺህ 224 ተማሪዎች መካከል ፈተና የወሰዱት 110 ሺህ 566 ሲሆኑ ከእነዚህም ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበው ወደ ቀጣይ 7ኛ ክፍል የተዛወሩ 70 ሺህ 584 ወይንም 63.8 በመቶ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የ8ኛ ክፍል ውጤት በትምህርት ቤት ደረጃ ሲገለፅ 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተመሪዎችን ማሳለፍ ሲችሉ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን አቶ አብዮት አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲያሳልፉ 81 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል ሀላፊው።
በአጠቃላይ ክልላዊ ውጤቱ ከአምና የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ8ኛ ክፍል 3 በመቶ ማነሱ የተገለፀ ሲሆን በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል አምና ክልላዊ ውጤት 56 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2018 ደግሞ 63 ነጥብ 84 እንደሆነም አስረድተዋል።
የ8ኛ ክፍል ውጤት
https://se.ministry.et/#/result
የ6ኛ ክፍል ውጤት
https://se6.ministry.et/#/result
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia