ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በአዲስ አበባ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በአዲስ አበባ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በአዲስ አበባ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደገለጸው፣ አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች