በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዴኦ ዞን፣ ዲላ ከተማ ጪጩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቢቲ ብርሃኑ የተባለ ወጣት በፌዴራል ፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክ…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዴኦ ዞን፣ ዲላ ከተማ ጪጩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቢቲ ብርሃኑ የተባለ ወጣት በፌዴራል ፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ወጣቱ ገና ከተሞሸረ 3 ወር ብቻ እንደሆነው ጠቁመዋል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጪጩ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ ግድያው የተፈጸመው ትናንት በፌዴራል ጉምሩክ ኬላ ከሚገኘው አካባቢ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወጣቱ እየተዝናና ባለበት ወቅት ነው።
የወጣቱ ሕይወት ያለፈው የፌዴራል ፖሊስ አባል በተኮሰበት ጥይት መሆኑንም ምንጩ ገልጸዋል።
የግድያው ምክንያት በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የገለጹት ምንጩ፣ "በኮንትሮባንድ ምክንያት ነው" ሲባል መስማታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የወጣቱ ሕይወት ማለፉ በአካባቢው ከተሰማ በኋላ ለሰዓታት አለመረጋጋት መከሰቱን ሌላ የጪጩ ነዋሪ ገልጸዋል። በአካባቢው ተኩስና የተወሰነ ረብሻ መከሰቱንም ጠቁመዋል።
የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ ፖሊስ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ትልልቅ አባቶች በጉዳዩ ዙሪያ በመስራት ሁኔታውን ማረጋጋታቸውንና ሰላም መስፈኑን ምንጩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከጌዴኦ ዞንና ከዲላ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጓል። ሆኖም ስልክ ባለመነሳቱና "መረጃውን አጠናክረን እናሳውቃለን" በሚል ምላሽ በዚህ ዘገባ የፖሊስ ተጨማሪ ማብራሪያ አልተካተተም።
የዲላ ከተማ ፖሊስ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ፣ ወጣት አቢቲ ብርሃኑ ሕይወቱ ማለፉን ገልጿል ነገር ግን ምንም ስለ ጉዳዩ የማያብራራና ግልጽ የማያደርግ መረጃ ካጋራ በኋላ ግድያውን ፈጽሟል የተባለውን ሳጅን ትንሳኤ ደጀኔ የተባለው ግለሰብ ፍርድ ቤት መቅረቡን ዛሬ አመሻሹን አሳውቋቃ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወጣቱ ሕልፈት ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ማጣራቶችን በማድረግ መረጃውን የሚያቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia