ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ትራምፕ ለእያንዳንዱ አዋቂ አሜሪካዊ 5,000 ዶላር እንሰጣለን አሉ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ትራምፕ ለእያንዳንዱ አዋቂ አሜሪካዊ 5,000 ዶላር እንሰጣለን አሉ።
ትራምፕ ለእያንዳንዱ አዋቂ አሜሪካዊ 5,000 ዶላር እንሰጣለን አሉ።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ኅዳር ወር ላይ በሚካሄደው የአማካይ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች የተወካዮች ምክር ቤቱንና ሴኔቱን ካሸነፉ ለእያንዳንዱ አዋቂ አሜሪካዊ ዜጋ 5,000 ዶላር እንዲያገኝ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።

የአማካይ ዘመን ምርጫ ማለት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከተመረጠ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄድ ምርጫ ነው። በዚህ ምርጫ ፕሬዝዳንት አይመረጥም፤ ይልቁንም የሕግ አውጪዎች፣ ማለትም የኮንግረሱ የተወካዮች ምክር ቤትና የሴኔት አባላት ይመረጣሉ። ይህም የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ በኮንግረስ ያለውን ቁጥርና ተፅዕኖ እንዲያጠናክር ወይም እንዲያጣ የሚያደርግ ምርጫ ነው።

ትራምፕ ሪፐብሊካኖች ካሸነፉ ለአዋቂ አሜሪካዊያን 5000 ዶላር እንሰጣለን ያሉት በቴክሳስ ዳላስ በተካሄደ የሪፐብሊካን ፓርቲ ጉባኤ ላይ ነው።

ይህ ገንዘብ ግን በአሜሪካ ውስጥ ብቻ እንደሚውል ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ እቅዱ በምን መንገድ እንደሚፈጸምና ገንዘቡ ከየት እንደሚገኝ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።

ወደ 270 ሚሊዮን የሚጠጉ አዋቂ አሜሪካውያን እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ለእያንዳንዳቸው 5,000 ዶላር መስጠት ወደ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ያስከትላል።

የትራምፕ ሀሳብ ከዴሞክራቶች ትችት የገጠመው ሲሆን፣ አንዳንድ ባለሙያዎችም እቅዱ በሕግ እንዴት ሊተገበር እንደሚችል ጥያቄ አንስተዋል።

ሌሎች ግን እንደ ግብር ቅነሳ ባሉ ሕጋዊ እርምጃዎች ሊተገበር እንደሚችል ይገልጻሉ።
ትራምፕ ከዚህ በፊትም ከቀረጥ ገቢ የሚሸፈን 2,000 ዶላር ለአሜሪካውያን ለመክፈል ሀሳብ አቅርበው ነበር።

ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች