ነጻ ኤግዝቢሽን
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ነጻ ኤግዝቢሽን
ከ20 በላይ የአሜሪካ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት የትምህርት ኤግዝቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኤጁኬሽን ዩኤስኤ (EducationUSA) የምክር ማዕከል ከዓለም አቀፉ የህብረተሰብ ትምህርት ቤት (ICS) ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የአሜሪካ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት የትምህርት ኤግዚቢሽን ያዘጋጃሉ።
ኤጁኬሽን ዩኤስኤ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር ከ175 በላይ ሀገራት በሚገኙ 430 የምክር ማዕከላት በኩል የአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርትና የፋይናንስ ድጋፍ እድሎችን ለተማሪዎች የሚያስተዋውቅ አውታር ነው።
ምንም እንኳን ራሱ ቀጥተኛ የስኮላርሺፕ አቅራቢ ባይሆንም እውቅና ያላቸው የአሜሪካ የትምህርት ተቋማት የሚሰጧቸውን የትምህርት እና የፋይናንስ ድጋፍ እድሎች ተማሪዎች እንዲያገኙ ያመቻቻል።
ኤግዚቢሽኑ የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. (September 19, 2026) ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት በICS ግቢ https://maps.app.goo.gl/3zggp33vSMqKD4iy8 ይካሄዳል።
በዚህም በአሜሪካ ፦
- የመጀመሪያ ዲግሪ፣
- የሁለተኛ ዲግሪ፣
- የሦስተኛ ዲግሪ ለመማር የሚፈልጉ ተማሪዎች ከተቋማቱ ተወካዮች ጋር በቀጥታ የመገናኘት እድል ያገኛሉ።
ኤግዚቢሽኑ ምንም አይነት ክፍያ የማይከፈልበት #ነፃ ሲሆን ለማንኛውም ፍላጎት ላለው ተማሪ ክፍት ነው። በዕለቱ በአካል ለመገኘት የሚፈልጉ ተማሪዎች ግን አስቀድመው በኦንላይን ቅጹ መመዝገብ አለባቸው።
ለመመዝገብ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc4WIhG79g0jMT896x3-RTGzwJsoGlY3lovzh9K_EKi4lXxbw/viewform
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም
Via @tikvahethmagazine