" አሁንም ገና በጣም ብዙ ወደ ኋላ ቀርተናል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የአእምሮ ሀኪሞች ያስፈልጉናል " - ፕሮፌሰር አታላይ አለም
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" አሁንም ገና በጣም ብዙ ወደ ኋላ ቀርተናል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የአእምሮ ሀኪሞች ያስፈልጉናል " - ፕሮፌሰር አታላይ አለም
የኢትዮጵያ የአእምሮ ሀኪሞች ማህበር 13ኛውን ዓመታዊ ጉባኤ " ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) ለተደራሽ እና ጥራት ላለው የአእምሮ ጤና እንክብካቤ መጠቀም " በሚል መሪ ሃሳብ አካሂዷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመድረኩ ተገኝቶ ከማህበሩ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አታላይ አለም ጋር ቆይታ አድርጓል።
Q. በፊት እና አሁን የኢትዮጵያ የአእምሮ ሕክምና ሁኔታ ምን ያህል ተለውጧል?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም ፦
" ከ20 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ያላት የአእምሮ ሀኪሞች ቁጥር 9 ነበር። አሁን ላይ ከ230 እስከ 240 የሚደርሱ ባለሙያዎች አሉ።
የሕክምና አገልግሎቱ ይሰጥ የነበረው በአዲስ አበባ ብቻ ስለነበር ታካሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለበርካታ ቀናቶች ተጉዘው ይመጡ ነበር። ይህ አሁን ቀርቷል። በሁሉም ክልሎች አገልግሎቱ ይሰጣል።
ይሁን እንጅ በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሠረት አሁንም ገና በጣም ብዙ ወደ ኋላ ቀርተናል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የአእምሮ ሀኪሞች ያስፈልጉናል። "
Q. የአእምሮ ሕክምና አገልግሎት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በበቂ ሁኔታ ደርሷል ?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" በእኛ ሀገርም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች የአእምሮ ሕክምና ለሕብረተሰቡ በደንብ የተዳረሰ አይደለም። "
Q. በተለይ በገጠር ያሉ ሰዎች የአእምሮ ጤና አገልግሎትን ለማግኘት ያላቸው እድል ምን ይመስላል?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" በገጠሩ አካባቢ መደበኛው የሕክምና አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ባይደርስም፣ አሁን ላይ ሞባይል ስልክ የሌለው ሰው ስለሌለ፣ ቴክኖሎጂው ከመደበኛው ሕክምና በተሻለ ደረጃ አገልግሎቱን ተደራሽ ያደርገዋል ብለን ነው የምናምነው። "
Q. ታዲያ AI የሰውን ቀጥተኛ ግንኙነትና ርህራሄ በሚፈልገው የአእምሮ ሕክምና ውስጥ እንዴት ሊጠቅም ይችላል?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" እሱን ነው አሁን እየተሞከረ ያለው። ከካናዳ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊቅ የሆኑ ሰዎችን ጠርተናል፣ ያላቸውን ልምድ እንዲያካፍሉን።
እንዴት ርህራሄ ባለው መንገድ ህመምተኛው ባለበት ሁኔታ ገብቶ አርቲፊሻል ኢንተለጀንሱ እንዴት ሊረዳ ይችላል ? የሚለው ትልቁ ውይይት የሚጠይቅ እና ገና በመጎልበት ላይ ያለ አዲስ አሠራር ነው። በሂደትም ወደዚያ ደረጃ ይመጣል ተብሎ ነው የሚታመነው። "
Q. AI የምዕራባውያንን ባህል ያንጸባርቃል ይባላል ? ከኢትዮጵያ ባህልና ቋንቋ ጋር እንዴት ሊስማማ ይችላል ?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" እያንዳንዱ ባህልና ቋንቋ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንዴት ሊቃኝ እንደሚችል እና ማሽኑ የእያንዳንዱን ቋንቋ፣ ባህል እንዲሁም አባባሎች እንዴት ሊማር እንደሚችል ትልቅ ሥራ የሚጠይቅ ነው፤ በአሁኑ ወቅትም በዚህ ላይ ትልልቅ የምርምር ሥራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። "
Q. የአእምሮ ጤና ከሌሎች የሕክምና ዘርፎች አንፃር በቂ ትኩረት እያገኘ ነው?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" ከሌላው የሕክምና ዘርፍ አንፃር ብዙ ትኩረት የተሰጠው አይደለም፤ ይህም ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ የሚከሰት ነገር ነው።
ስለዚህ ግንዛቤውን ለማዳበር ብዙ ምርምሮች እያደረግን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ፕላነሮች ጋር እየተገናኘን ነገሩ የተሻለ ትኩረት እያገኘ መጥቷል። "
Q. በቀጣይ የአእምሮ ጤና ሕክምናን ለማሻሻል ምን እየተሠራ ነው?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም ፦
" ማህበሩ ከጤና ጥበቃ ጋር በመሆን የአምስት ዓመት የአእምሮ ሕክምና ስትራቴጂ ለማውጣት እየሠራን ነው።
የሰው ኃይል ለማፍራትም አስተማሪዎች ስለሆን እየሠራን ነው። በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ብዙ የአእምሮ ሕክምና አገልግሎት ሰጪዎች አሉ። ግን በቂ አይደሉም። ግን እያስተማርን ነው። "
Q. ሶሻል ሚዲያ በአሁኑ ጊዜ በተለይ በወጣቶች የአእምሮ ጤና ላይ ምን ተፅዕኖ እያሳደረ ነው?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" ሶሻል ሚዲያ በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ጉዳቶችን እያስከተለ ነው። ሶሻል ሚዲያ ለበጎም ለክፉም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቢሆንም፣ አሁን ላይ በተለይ በወጣቶች ላይ የአእምሮ ሕመም እያስከተለ መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል። "
Q. ታዲያ ሰፊ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት የዲጂታል ሚዲያ ሕግ አያስፈልገንም ?
💬 ፕ/ር አታላይ አለም፦
" በትክክል! በጣም ያስፈልገናል።
አሁን ላይ ሀገራችን የዲጂታል ዓለሙን ለመቀላቀል ብዙ ሩጫ አለ። ግን ከዚሁ ጋር ባልተናነሰ ደግሞ እንዴት በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለብን በደንብ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ማስመር እፈልጋለሁ። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia