ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አቶ ኢሳያስ ጅራ ዳግም በሀላፊነት ተመረጡ !

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አቶ ኢሳያስ ጅራ ዳግም በሀላፊነት ተመረጡ !
አቶ ኢሳያስ ጅራ ዳግም በሀላፊነት ተመረጡ !

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አቶ ኢሳያስ ጅራ ዳግም ተመርጠዋል።

አቶ ኢሳያስ ጅራ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸው አይዘነጋም።

ከደቂቃዎች በፊት ከተሰጡ 88 ድምፆች አቶ ኢሳያስ ጅራ 81 ድምፆችን በማግኘት በድጋሜ ሊመረጡ ችለዋል።

ይህንንም ተከትሎ አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሚቀጥሉት አራት አመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው የሚያገለግሉ ይሆናል።

አቶ ኢሳያስ ጅራ በካፍ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና በፊፋ ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ።

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ከምርጫው መጠናቀቅ በኃላ በስልክ “ የእንኳን ደስ አለህ “መልዕክታቸውን አጋርተዋል።

በዛሬው ምርጫ ላይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን :-

- የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

- የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ መስቀሌ በመሆን ተመርጠዋል።

Via @tikvahethsport    

ተዛማጅ ታሪኮች