ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፖስታ ጥቅሎች እና የኢ-ንግድ ዕቃዎች የሎጅስቲከስ ማዕከል ለማድረግ ያለመው ታላቅ አህጉራዊ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፖስታ ጥቅሎች እና የኢ-ንግድ ዕቃዎች የሎጅስቲከስ ማዕከል ለማድረግ ያለመው ታላቅ አህጉራዊ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!
በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) እና በኢትዮጵያ ፖስታ ትብብር የተዘጋጀው "የአፍሪካ ቀጠናዊ የትራንስፖርት አውደ ጥናት" (Regional Transport Workshop for Africa) ከ ነሐሴ 20 ቀን ዓ.ም 2018 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በይፋ ተከፈተ። ይህ ታላቅ መድረከ በአፍሪካ የሚገኙ የፖስታ ኦፕሬተሮች አመራሮችን እና በአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮችን ጨምሮ የንግድ እና የአህጉራዊ ትስስር ቁልፍ ተዋናዮችን በአንድ ያሰባሰበ ነው።
ይህ አውደ ጥናት ሶስት ግዙፍ ተቋማትን ያገናኘ ነው- በ1874 እ.ኤ.አ. የተመሰረተና የ192 አባል ሀገራትን ኔትዎርክበማስተባበር ዓለም አቀፍ የፖስታ ህጎችንና ትብብርን የሚመራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ኤጀንሲ የሆነው ዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU)፣ በኢ-ኮሜርስ እና ፈጣን ጥቅሎች የመጨረሻ መዳረሻ አገልግሎት አቅራቢ (Last-Mile delivery service provider) የሆነውና ራሱን በከፍተኛ ደረጃ እያዘመነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፖስታ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ትልቁ እና በዓለም አቀፍ የካርጎ ሎጅስቲከስ አቅሙ በስፋት የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናቸው፡፡
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረከ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የፖስታ ተቋማት ተወካዮች፣ የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች እና የሎጅስቲከስ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ውይይቶቹ የአፍሪካን የፖስታ እና ኢ-ንግድ ዕቃዎች ትራንስፖርት እና የአቅርቦት ሰንሰለት መሠረተ-ልማት ማዘመን ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ በተለይም በአየር ካርጎ ሎጅስቲከስ እና በመሬት ላይ ስርጭት መካከል ያለውን ቅንጅት በማጠናከር ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ ለማድረግ ያለመ ነው። እንደዚሁም ይህ አውደ ጥናት በአህጉራችን አፍሪካ የሚገኙ የቀጠናዊ ትስስሮችን ማሳደግ እንዲሁም በፖስታ ቅብብሎሽ ሰንሰለት እና የመልዕከት ደህንነት ረገድ ተፎካካሪነትን ማጎልበት ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
በተጨማሪም ይኸው መድረክ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የትራንስፖርት ህብረት በጠንካራ መሰረት ላይበመትከል፣ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
በመከፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ፣ የፖስታው ዘርፍ እያደረገ ያለውን ስትራቴጂያዊ የለውጥ ጉዞ በማንሳት፤ አባል ሀገራት ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ እና የመጨረሻ ማይል የዕቃ አቅርቦት ቴክኖሎጂዎችን በማስተሳሰር ለተገልጋዮች የላቀ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል። በመድረኩም የፖስታ አገልግሎት ከተራ የደብዳቤ ልውውጥ አልፎ ለአህጉሪቱ ንግድ፣ ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና ለድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ ዋነኛ የሎጂስቲክስ ሞተር መሆኑ ጎልቶ ተነስቷል።
በተመሳሳይ የዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የልማት እና ትብብር ዳይሬከተር ሚስተር ሙቱዋ ሙቱሲ፣ አውደ ጥናቱ አፍሪካ በቀጠናዊ ንግድ ያላትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። አያይዘውም፣ ኢትዮጵያ ፖስታ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ላስመዘገበው ስኬትና ሽልማት አድናቆታቸውን ገልጸው፤ የተቋሙ ስኬታማ የለውጥ ጉዞ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ መሆኑን አብራርተዋል።
ከፖስታ አገልግሎት መሻሻል ባሻገር፣ የዚህ ስትራቴጂያዊ መድረከ ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀዳሚ የሎጅስቲከሰ ማዕከል (Logistics Hub) አድርጎ መገንባት ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለውን ሰፊ ዓለም አቀፋዊ የአየር ትስስርከኢትዮጵያ ፖስታ ሀገር አቀፍ እና ቀጠናዊ የቅርንጫፍ ኔትዎርክ ጋር በማስተሳሰር፤ ኢትዮጵያ የአህጉሪቱን የኢ-ኮሜርስ ዕድገት ለመምራት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊነት ለማሳለጥ ምቹ ቁመና ላይ እንደምትገኝ አውደ ጥናቱ አጉልቶ ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።
መድረኩ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በተግባራዊ ጉብኝት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ግዙፍ የካርጎ ማዕከል እና የኢትዮጵያ ፖስታን ዓለም አቀፍ የፖስታ ልውውጥ ማዕከል በመጎብኘት፤ ኢትዮጵያ ለወደፊቱ የአፍሪካ ሎጅስቲከስ ዘርፍ የዘረጋችውን የተቀናጀ መሠረተ-ልማት በአካል የሚመለከቱ ይሆናል።
@ethiopiapost