" እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ። ዝርፊያም አለው። ዋናው ፍላጎት መሬት ማስለቀቅ ነው " - የክልሉ ምክር ቤት አባል
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ። ዝርፊያም አለው። ዋናው ፍላጎት መሬት ማስለቀቅ ነው " - የክልሉ ምክር ቤት አባል
በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት በሚደርስበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጥቃቱ ባለመቆሙ ሰሞኑንም ንጹሐን መገደላቸውን፣ ንብረት መዘረፉን አንድ የዞኑ አመራርና የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አመራሩ በሰጡን ቃል፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላናና ሱሮባርጉዳ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ መሆናቸውን አስረድተዋል።
መላኩ ማዝሬ የተባሉ ግለሰብ ከብቶች በማሰማራት ላይ በነበሩበት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከጋላና ወረዳ ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ዘልቀው በገቡ የጉጂ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግለሰቡ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ማረጋገጣቸውንም አስረድተዋል።
ሌላኛው የቀበሌው ነዋሪ፣ የግድያ ጥቃት በታጣቂዎቹ ከብቶች መነዳታቸውን ገልጸው፣ "ከብቶቹ የተዘረፉት ከምዕራብ ጉጂ ጋላና ወረዳ ጋላና መጣሬ ልዩ ስሙ ቡልቶ ዳልጀሳ መንደር በሚኖሩ ታጣቂዎች ነው" ብለዋል።
"ታጣቂዎች አንድ ሰው ገድለው የአንድ በረት ከብቶችን ዘርፈዋል። በነሐሴ ወር ተከታታይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። ሐምሌ 30/2018 የኬሌ ቀበሌ አስተዳደር ነዋሪ የሆነው ከድር አብዱ በጎርካ ወረዳ ጋሙሌ ቀበሌ መንገድ ላይ ተገድሏል" ተብሏል።
እንዲሁም፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከከጋላና ወረዳ ሻሞሌ ሽዳ ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጋሙሌ ዘልቀው በገቡ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነሐሴ 22/2018 ዓ/ም፣ መሐመድ ደረሱ የተባሉ የዶርባዴ ቀበሌ ነዋሪ መገደላቸውም ተመልክቷል።
በዞኑ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ በሚፈጸሙ ጥቃት በርካቶች መገደላቸው የሚገለጽ ሲሆን፣ የኮሬ ህዝብ የፓርላማ ተወካዩ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፣ ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከዚህ ቀደም ነግረውናል።
የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?
በቅርቡ የተመረጡት የክልሉ ም/ቤት አባል አቶ ዴያሞ ዳሌ ዛሬ በሰጡን ቃል፣ ሰሞኑንም በተፈጸመ ጥቃት አርሶአደሮች መገደላቸውን ገልጸዋል። "ጥቃቱ የሚቆምበት እድል አልተገኘም። የፌዴራል መንግስት ትኩረት ካልሰጠው የሚቆም አይደለም" ብለዋል።
ጥቃቱ ወደ 10 ዓመታት ማስቆጠሩን፣ ከ10 በላይ ቀበሌዎች የጥቃቱ ተጋፋጭ እንደሆኑ ተናግረዋል። "ወረራ ተፈጽሞ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። የመንግስት ጸጥታ የማስከበር ሁኔታ ላልቷል" ብለዋል። በአካባቢው "የሸኔ" ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እንዳለ፣ ከወሰን አከላል ጋር በተያያዘ በነዋሪዎች መካከልም የበቀል ጥቃት እንደሚስተዋል ገልጸዋል።
አክለው፦
"አሁን ምዕራብ ጉጂ የሚባለው ዞን ገላና እና ሱሮባጉርዳ የሚባሉት ወረዳዎች አብዛኛው ክፍል አማሮ ወረዳ ውስጥ የነበሩ ናቸው። በኋላ የብሔረሰብ አከላለል ሲመጣ አማሮ ወረዳ ሁለት ቦታ ተከፈለ።
ጉጂ ያለበት አካባቢ ገላና ወረዳ ሆነ። የተቀረው ኮሬ ብቻ ያለበት ተብሎ የሚጠራው አማሮ ወረዳ ተብሎ ቀጥሎ አሁን ኮሬ ዞን ሆነ። ያለው የፌዴራሊዝም ስርዓት እነዚህ ሲከፋፈሉ ቦታዎች ድንበር የማስመር Formal የሆነ ስርዓት የለውም። ምክክር ኮሚሽኑ ላይ የቀረበው አንዱ አጀንዳም ይሄው ነው።
አንዳንዴ በሪፈረንደም ተብሎ ይከለልና መሬቱ ይገፋል። በዚህ አካባቢም ብዛት ያለው ውሃ የሚመነጨው ኮሬ ዞን ነው። ውሃው ሂዶ የሚተኛባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለእርሻ አመቺ የሆኑ ናቸው፤ ስለዚህ አርሶረደሩ ወደዚያ አካባቢ ሲሄድ ይገደላል።
በተያያዘ፣ እዛ አካባቢ የተፈናቀለ ወጣት ስራ የለውም። ይህ ጥቃቱ እንዳይቆም ያደርጋል። ዛሬ እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፤ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ። ዝርፊያም አለው፤ ዋናው ፍላጎት መሬት ማስለቀቅ ነው።
ጉዳዩ ሁለት ክልሎች ላይ ስለሆነ የሚፈጠረው ባለጉዳይ መሆን ያለበት የፌዴራል መንግስት መሆን ሲገባው 'እናንተ ተነጋገሩ' እየተባለ ነው የሚተወው። ሰው የገደለ ሰው ለሕግ የማይቀርብበት ሁኔታ ነው ያለው። ችግሩ አሁን ያለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ነው። የሀገር ውስጥ ወሰኖችን እንደ ውጭ ድንበር ተደርጎ ሰው የሚጋደልበት ስርዓት ነው ያለን" ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉጂ ዞን በኩል ያሉ አመራሮችን ምላሽ ለማካተት ያደረገው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ ከሰጡ የምናቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia