" እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞቅ ያለና ልብን የሚነካ አቀባበል ያደረገልኝ የለም ! " - የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞቅ ያለና ልብን የሚነካ አቀባበል ያደረገልኝ የለም ! " - የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት ደማቅ መንፈሳዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
" የእንኳን ደህና መጡ " አባታዊ ንግግር ያደረጉት ቅዱስነታቸው " እርሶ ከሩቅ አገር ከልዑካኑዎ ጋር መጥተው አገራችንን ስለባረኩ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፤ ደስም ብሎናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጥንታዊያን አኃት አብያተ ክርስቲያናት እንደመሆናቸው መጠን በየጊዜው መገናኘትና መወያየት ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።
" ከአሥር ዓመት በፊት እኔና የሲኖዶስ አባላት በሕንድ አገር ተገኝተን ያደረግነውን ጉብኝት እናስታውሳለን። አሁንም ቅዱስነትዎ በኢትዮጵያ በሚኖሮት ቆይታ በጸሎትዎ አገራችንን እንዲያስቡልን አደራ እያልኩ፣ መላው ሊቃነ ጳጳሳትና ካህናት፣ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን፣በመምጣትዎ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እገልጻለሁ፤ መልካም ቆይታም እመኛለሁ " ብለዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በበኩላቸው " በዓለም ዙሪያ ባደረግኳቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞቅ ያለና ልብን የሚነካ አቀባበል ያደረገልኝ የለም። ዛሬም በካቴድራሉ የተደረገልኝ አቀባበል፣ የቀረበው ዝማሬና ክብር ልባችንን በጥልቅ ነክቶታል " ሲሉ ገልጸዋል።
በሁለቱ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ታሪካዊና መንፈሳዊ ትስስር በማስታወስም፣ በቀጣይ በሴሚናሪዎች ደረጃ የተማሪዎችና የመምህራን ልውውጥ በማድረግ በነገረ መለኮት፣ በባህልና በሥርዓተ አምልኮ ዘርፎች የጋራ ሥራን ለማጠናከር እንደሚሠራ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia